ቅንነት
Qenenet
ትራክ 7 · 6:27 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ቅንነት ተገኝቶብኝ አይደል
ጌታዬ እኔን የወደደው
ግን ከምህረቱ የተነሳ
ቆሜያለሁ ስሙን ላነሳ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ያለፈውን ዘመን ሲያስታውሰው ልቤ
በህልም ይመስለኛል ያለፍኩት በሃሳቤ
መልካሙን ቀን ያየ እግዚአብሔር የረዳው
ደግሞ ከፈል ይላል እንደ እኔ አይነቱ ሰው
መልካሙን ቀን ያየ እግዚአብሔር የረዳው
ደግሞ ከፍ በል ይላል እንደ እኔ አይነቱ ሰው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አጋዥ በሌለበት ደረቅ ምድረ በዳ
አጋዥ ትሆናለህ ብቻውን ለተጐዳ
የሃሩሩን ሙቀት በጥላህ ከልክለህ
ስንቱ ቀን ወጣብህ ስንቱ ተከለለ (፪x)
አዝማች · Chorus
ትከሻህ ለእኔ ሁሉ ምቹ ነው
ከፍ በል ምለህ ቀን ወጥቶልኝ ነው (፪x)
ከቶ አልሰጋም ምን እሆን ብዬ
እኖራለሁ ተደላድዬ (፪x)
እኖራለሁ ተደላድዬ (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
እንደትላንትናው መስሎት
ጠላቴ ቢወጣ ፈጥኖ (፪x)
በመንገዴ አንተ ቀድመሃል
ለጥያቄው መልስ ሰጥተሃል
ጥያቄው መልስ ሰጥተሃል (፪x)
አዝማች · Chorus
ከእንግዲህ ላልሰጋ ልቤም ላይፈራ
እግዚአብሔር አምላኬ ሆኗል ከእኔ ጋራ
በተከበበ ከተማ ምህረቱን ለእኔ አሰማ
በተከበበ ከተማ ምህረቱን ለእኔ አሰማ
ረዳቴ ከፍ ይበልልኝ (፬x)
በከበበው ከተማ ምህረቱን ለእኔ አሰማ (፪x)
ረዳትዬ ከፍ ይበልልህ (፬x)
በከበበው ከተማ ምህረቱን ለእኔ አሰማ (፪x)
ረዳትዬ ከፍ ይበልልህ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ