በውኃ ላይ ሄደ
Beweha Lay Hiede
ትራክ 1 · 6:05 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አዲስ አዲስ ነገር እኔን ለማስለመድ
ደግሞ አደረገ በውኃ ላይ መንገድ (፪x)
አዝማች · Chorus
በውኃ ላይ ሄዶ አሳይቶኛል (፪x)
ታዲያ እኔ እንዳልሄድ ምን ያስፈራኛል (፪x)
በውኃ ላይ መሄድ እሱ ከቻለ (፪x)
እራሱን ተማምኖ አንችሂን ነይ ካለ አንተን ና ካለ (፪x)
አልፈራም እኔም አልፈራም (፮x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እኔ ያየሁት ውሃውን አይደለም
ጌታ ይሁን ካለ የማይሆን የለም
በውኃ ላይ መሄድ አልችልም እያሉ
እኔስ ስራመድ አይተው ጉድ አሉ (፪x)
አዝማች · Chorus
በውኃ ላይ ሄዶ አሳይቶኛል (፪x)
ታዲያ እኔ እንዳልሄድ ምን ያስፈራኛል (፪x)
በውኃ ላይ መሄድ እሱ ከቻለ (፪x)
እራሱን ተማምኖ አንችሂን ነይ ካለ አንተን ና ካለ (፪x)
አልፈራም እኔም አልፈራም (፮x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ውሃውም ያው ነዉ ባሕሩም ያው ነዉ
እኔ ግን የያዝኩት የአምላኬን ቃል ነዉ (፫x)
እርሱ ነይ ካለ መሄድ የእኔ ነው (፪x)
ግራ ቀኝ አይቶ መፍራት ምንድን ነው (፪x)
እርሱ ና ካለ መሄድ የእኔ ነው (፪x)
ግራ ቀኝ አይቶ መፍራት ምንድን ነው
መፍራት ምንድን ነው (፪x)
ረገጥ አደረኩኝ ማዕበሉን በድፍረት
ለካስ ድምጽ ብቻ ነበረ ወይ ጩኸት (፬x)
. (1) .
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ