ወርቅም አይተካህም
Werqem Aytekahem
ትራክ 8 · 6:16 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አንተ ነህ ሰላሜ አንተ ነህ (፬x)
ወርቅም አይተካህ
ብርም አይተካህ
ወዳጅ አይተካህ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ጌትዬ ምን እልሃላሁ (፪x)
ሥምህን እባርካለሁ (፪x)
ብዙ ሰላም የሚመስል አለ በምድር ላይ
ከንቱ ነው ለጊዜው ታይቶ ይጠፋል
አንተ ግን የማይናወጥ ሰላም አለህ
ከቤትህ ዘለዓለም ደስታን ታጠግባለህ (፪x)
አዝማች · Chorus
ጌትዬ ምን እልሃላሁ (፪x)
ሥምህን እባርካለሁ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ጌታዬ ለእኔስ ልዩ ነህ ለዘለዓለም
የውስጤን የሚያውቅልኝ እንደ አንተ የለም
ሃሳቤን የልቤን ቀርበኸኝ ታውቃለህ
ከሩቁ መንገዴን አንተ ታቀናለህ (፪x)
ደስ ይለኛል በአንተ ጌታዬ
ሃሴትን ሞልተሃል በውስጤ (፪x)
አዝማች · Chorus
አንተ ብቻ በእኔ ላይ ጌታ (፬x)
ሌላ ሌላው ከንቱ ነው ሌላው
ሌላ ሌላዉ ሰነፍ ነው ሌላዉ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እኔ ጌታ ምለው ጌታ የሆነውን
ልቤ የፈቀደው የተቀበለውን (፪x)
ጌታ ነዉ (፰x)
አዝማች · Chorus
አንተ ብቻ በሰማይ ጌታ
አንተ ብቻ በምድር ጌታ (፪x)
ሌላ ሌላው ከንቱ ነው ሌላው
ሌላ ሌላው ሰነፍ ነው ሌላው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ