Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

በሰማይ

Besemay

ትራክ 4 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በሰማይ በምድር በፍፁም የለም አንተን የሚመስል (፪x)

በሰማይ በምድር በፍፁም የለም አንተን የሚመስል (፪x)

በደመናትም ላይ ይራመዳል

ፍጥረታትንም ሁሉ እርሱ ያዛል

ጥንቃቄ የተሞላ ጌታ

ፍፁም የለም እርሱን የሚረታ

ጥንቃቄ የተሞላ ጌታ

ፍፁም የለም እርሱን የሚረታ (፪x)

በሰማይ በምድር በፍፁም የለም አንተን የሚመስል (፪x)

ለዓለምና ለዘላለም

ይሄ ነው እግዚአብሔር የምንለው

መጀመሪያ መጨረሻ የለው

ፍጥረት ሁሉ ስራውን ያድንቀው

መጀመሪያ መጨረሻ የለው

ፍጥረት ሁሉ ስራውን ያድንቀው (፪x)

ስራህን ደግሞ ጥበብህን

ዝናህን ከሩቅ ሰማሁ

ስቀርብህ ከሰማሁት በላይ

ሆነህ አገኘሁህ (፪x)

ሁሉን አልፌ እሄዳለሁ

የሚቃወመኝ ከቶ ማነው

ሁሉን ሰብሬ እሄዳለሁ

ሰባሪው እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ነው (፪x)

አልፎ ሄዷል ከበሩ

አልፌ እሄዳለሁ

ንጉሡን ተከትዬ

መቼ አፍራለሁ (፭x)

አልፎ ሄዷል ከበሩ

አልፌ እሄዳለሁ

ንጉሡን ተከትዬ

መቼ አፍራለሁ (፭x)

እግዚአብሔርን የታመኑ ዓይናቸውን ያድሳሉ

እንደንስር በከፍታ ላይያዙ ይወጣሉ (፪x)

ይሄን . (1) .

በምንም ነገር ላይደርስብኝ

አስጥሎኛል ጌታ እግዚአብሔር

ጌታ እግዚአብሔር (፯x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ