ምን አለኝ ለአንተ
Men Alegn Leante
ትራክ 11 · 5:49 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ምን አለኝ ለአንተ እህህህ
የምከፍለው ነገር እህህህ (፪x)
ክበር ክበር የእኔ ጌታ ክበር (፬x)
ምን አለኝ ለአንተ እህህህ
የምከፍለው ነገር እህህህ (፪x)
ክበር ክበር የእኔ ጌታ ክበር (፬x)
ቁጥር 1 · Verse 1
እንደ ማለዳ ቀን እንደ ደመና
ሰማያትን ከድኗል የአንተ ምሥጋና
እኔም ጨምራለሁ እንደገና አሃሃ (፬x)
እኔስ ስለአንተ ባወራ ባወራ አሃሃሃ
ተዓምራቶችህ በየተራ አሃሃ
እንኳን ቆጥሬ ልዘልቀው (፪x)
ተመስገን ብዬ አልችለው
ተመስገን ብዬ አልችለው (፪x)
አዝማች · Chorus
አድነከኛል እና አከብርሃለሁ (፪x)
ምሥጋናዬን ለአንተ አበዛለሁ (፬x)
አድነከኛል እና አከብርሃለሁ (፪x)
ምሥጋናዬን ለአንተ አበዛለሁ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ኧረ እኔስ እንዴት ልበል ዝም (፪x) አልቻልኩም
ላመስግንህ አምላኬ ዘወትር
ምህረትህን እያሰብኩ ለእኔ ያደረከውን
ለእኔስ እጅግ በዛ የአንተ ውለታ (፪x)
ምሥጋናን ልሰዋ ለረዳኸኝ ጌታ (፪x)
ለእኔስ እጅግ በዛ የአንተ ውለታ (፪x)
ምሥጋናን ልሰዋ ለረዳኸኝ ጌታ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ