Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ፀሐይ አትጠልቅም

Tsehay Atetelqem

ትራክ 9 · 5:54 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ያየሁትን አይቼ (ኧረ እንዴት)

ኧረ እንዴት ልመለስ ፈርቼ (ያየሁትን)

ያየሁትን አይቼ (ኧረ እንዴት)

ኧረ እንዴት ልመለስ ፈርቼ (፪x)

ሰምቼ ወጥቻለሁ የተናገረኝን

መሃል ላይ ደርሼ ግራ አይገባኝም

ሰምቼ ወጥቻለሁ የተናገረኝን

ዮርዳኖስ ቢሞላ ግራ አይገባኝም

የተናገረኝ ያለኝን ሳላይ

ፀሐይ አትጠልቅም ከቶ በእኔ ላይ (፪x)

(እሰይ)

ጭንገፋ በዘመኔ በእኔ እንዳይሰራ

እግዚአብሔር አምላኬ ቆሟል ከእኔ ጋራ (፪x)

በእኔ የተጀመረው ሥራ እግዚአብሔር ነው

የሚያስተጓጉለኝ እርሱ የትኛው ነው

በእኔ የተጀመረው ሥራ እግዚአብሔር ነው

የሚያስተጓጉለኝ እርሱ የትኛው ነው

ሰው አይደለም የተናገረኝ

እግዚአብሔር ነው ትወርሻለሽ ያለኝ

ሰው አይደለም የተናገረኝ

እግዚአብሔር ነው ትወርሳለህ ያለኝ (፪x)

ተናግሮ ማድረግ (ጌታ) ጌታ ከቻለ (አሜን)

ልቤ በእርሱ ላይ ዛሬም ታመነ (ተናግሮ)

ተናግሮ ማድረግ (እርሱ) ጌታ ከቻለ (አሃሃ)

ልቤ በእርሱ ላይ ዛሬም ታመነ

ከአፉ ቃል በቀር ከተናገረው

በእኔ ላይ አይሆንም/አይሰራም ጠላቴ ያለው (፬x)

ይጨምር እሳቱ ሰባት እጥፍ ቢነድ

እግዚአብሔር ለእኔ በዚያ አለው መንገድ (፫x)

የተናገረኝ

(ያለኝን ሳላይ) ያለኝን ሳላይ

(ፀሐይ አትጠልቅም) ፀሐይ አትጠልቅም

(ከቶ በእኔ ላይ) ከቶ በእኔ ላይ (፪x)

በጨለማው ላይ ብርሃን ይብራ ያለው

እግዚአብሔር እርሱ ብርሃን ነው (፬x)

በጨለማው ላይ ብርሃን ይብራ ያለው

እግዚአብሔር እርሱ ብርሃን ነው (፬x)

የተናገረኝ

(ያለኝን ሳላይ) ያለኝን ሳላይ

(ፀሐይ አትጠልቅም) ፀሐይ አትጠልቅም

(ከቶ በእኔ ላይ) ከቶ በእኔ ላይ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ