Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

በስራህ

Beserah

ትራክ 3 · 6:09 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በስራህ ሁሌ ትክክል ቃልህን ስትናገር እውነት

በልቡ እንደአንተ ትሁት

እንደአንተ አላየሁም የሚነገርለት

እንደአንተ አልሰማሁም የሚባልለት

እንደአንተ አላየሁም የሚነገርለት

እንደአንተ አልሰማሁም የሚባልለት (፪x)

ከፍ በል የሚመስልህ የለህም (፬x)

ተሳስተሃላል አስተካክል ማን ይልሃል

አንድም ቀን በስራህ ማን አምቶሃል (፪x)

ማንም ተሟግቶ አንተን አይረታም

የመማለጃ ብዛት ፈቀቅ አያደርግህም (፪x)

እውነተኛ እንደአንተ ማነው

ሁልጊዜ ትክክል ኧረ እንዳንተ (፪x)

እንዳንተ አላየሁም የሚነገርለት

እንዳንተ አልሰማሁም የሚባልለት

እንዳንተ አላየሁም የሚነገርለት

እንዳንተ አልሰማሁም የሚባልለት (፪x)

ከፍ በል የሚመስልህ የለህም (፬x)

ስምህን ላከብር ፊተኛ ሆኛለሁ

በመንገዶችህ ንጹህ እንደአንተ አላየሁ

በመንገዶችህ ንጹህ እንደአንተ አላየሁ (፪x)

ኧረ አምላኬ ንጉሤ አጣሁልህ

ልቤ ወደደህ ጌታዬ ተማርኮብህ (፪x)

አምላኬ ሰፊ ነህ ከአእምሮዪ በላይ

እኔ አልገምትህ የሁሉ የበላይ (፪x)

ከምልህ በላይ በላይ (፬x)

ለዘለዓለም ብሩክ ስምህ ይባረክ (፬x)

ለዘለዓለም ብሩክ ስምህ ይባረክ (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ