Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ጉበኛ ነኝ

Gubegna Negn

ትራክ 5 · 5:38 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የተስፋውን ቃል ከሩቅ አይተው እንደተሳለሙት

አይደለም የእኔ ጊዜ ተሰጠኝ እድል የማየት

ሁሉን ወራሽ ባደረገው በዚህ ዘመን ተናገረኝ

ቅባቴን ለክብር አድርጐታል ምሳሌውን ልፈልግ (፪x)

በማየው ነገር አልረካም አዲስን ነገር ስፈልግ

በራሴ ዘመን አካሄዴ ከአንተ ጋራ አድርጌ ልለፍ (፪x)

ጉበና ነኝ በቅጥር ላይ ልቆም ተነሳሁ

አስጨናቂውን በጭንቅ ላስለቅቀው (፪x)

ታማኝ አድርገህ የቆጠርከኝ

የቤትህ አገልጋል እንድሆን ሾምከኝ

የልብህን ሃሳብ በእኔ ለመፈጸም

የእኔ ሁኔታ አንተን አላገደም (፪x)

ታዲያ ዘመኔን ለአንተ ብያለሁ

እንድትገዛም እኔ ፈቅጃለሁ (፪x)

በእኔ ላይ ጉዳይ አለህ

ስትጠራኝ አላማ አለህ

ክብርህን/ልጅህን ልትገልጽ በእኔ

ወደሃል ጌታ በዘመኔ (፪x)

ለአላማዬ ጨካኝ እርስቴን የማልሸጥ

ጥፋትን በመጸየፍ በጽድቅ እየኖርኩኝ

ተነሳሁ ፊትለፊት ጠላቴን ልገጥመው

የወሰደውን ላስመልስ ምርኮን ልበዝብዘው

ተነሳሁ ፊትለፊት ጠላቴን ልገጥመው

የወሰደውን ላስመልስ ምርኮን ልበዝብዘው (፪x)

የኪዳን ሰው ተናጣቂ ጦረኛ ነው

ለበራለት እውነት ወደ ኋላ የማይል ነው

ለዓለም ክብር ተመሳስሎ ዐይኖርም

በእርሱ ላይ ያለውን ፀጋ አይስደፍርም (፪x)

የጠላቴን እጅ ዘርግቻለው ላልመልሰው

ድል የራሴ ነው እጄም ይረታል

ነገር ልፈላልገው (፪x)

ለትውልድ ተሟጋች እኔ እያለሁ

አይሰራም ከእጄ አያመልጥ ጠላቴ

የናፈቀውን አይወርስም (፫x)

አይወርስም አይወርስም

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ