በንሰሃ እንመለስ
Beneseha Enemeles
ትራክ 3 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በንሰሃ ለመመለስ
ወደ ዙፋንህ ለመድረስ
መጥተናል ተቀበለን
በደላችንን ይቅር በለን (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
የቤትህን ተድላን ሰላም ተቀምተን
ከፍ ካድረከን ከጉያህ ውስጥ ወተን
ጠላትህ ረጋግጦ ብዙ አጐሳቁሎናል
በምህረትህ ጐብኘን ፊትህ ይሻለናል
የዓለምን ምርኩዝ ኀጢአት ተደግፈን
በስራ ሳንለይ እንዲሁን በአፋችን
አሁን ምኑ ላይ ነው የእኛ ሕይወታችን
በጌታ ቤት ሆነን እየተገፋፋን
አዝማች · Chorus
በንሰሃ ለመመለስ
ወደ ዙፋንህ ለመድረስ
መጥተናል ተቀበለን
በደላችንን ይቅር በለን (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ይብቃን አሁን ይብቃን እንደሬት ይምረረን
ኀጢአትን እንጥላው በንሰሃ ታጥበን
እንደጌታ ያለ የትም አናገኝም
አይተነው የለም ወይ ቆሻሻውን ዓለም
በስም ክርስትና ብለን ተሸፍነን
በቃላት ታጅበን ለሚያየን ሰው መስለን
ምንም አልተለወጥን ገባ ብሎ ለአየን
ሌላ ስም የለንም ይህ ነው ታሪካችን
አዝማች · Chorus
በንሰሃ ለመመለስ
ወደ ዙፋንህ ለመድረስ
መጥተናል ተቀበለን
በደላችንን ይቅር በለን (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
"እንደ ምህረትህ ብዛት
እንደቸርነትህ መጠን
ለአምጻችንና ለኀጢአታችን ፍሬ
አሳልፈህ አትስጠን"
ዘር ቀለምን ለየን የእኛ ጉድ አያልቅም
አንድ ያደረከንን ጌታ ለዘለዓለም
ዐይናችን ጨልሞ ከፋፍለን ብናይም
ባሪያ ጨዋ ብሎ ቃሉ አይለያየንም
ክርስቶሥን ለብሶ አይሁድ ግሪክ የለም
የጸና ቃል አለን ማንም አይሽረውም
እንመለስ አሁን ጌታ መሃሪ ነው
እርሱ ይቅር ሊለን ሁሌም ዝግጁ ነው
አዝማች · Chorus
በንሰሃ ለመመለስ
ወደ ዙፋንህ ለመድረስ
መጥተናል ተቀበለን
በደላችንን ይቅር በለን (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
አጣፍጠን ብንዘምር አንደበትን ስለን
ጌታ ሚፈልገው መቀደሳችንን
ድምጹን እናዳምጠው እስኪ እንተላለፍ
በስራ እንለይ በቃል ከመለፍለፍ
የድፍረት ኀጢአት አናፍርም ስንሰራ
እንደ ኤሊ ልጆች በነውር ስንኮራ
ምክር ግሳጼንም እንሰማም ብለናል
በመስዋዕቱ ሥጋ ልባችን ደንድኗል
አዝማች · Chorus
በንሰሃ ለመመለስ
ወደ ዙፋንህ ለመድረስ
መጥተናል ተቀበለን
በደላችንን ይቅር በለን (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ