ወረደ አምላኬ
Werede Amlakie
ትራክ 2 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በአፍላ ልጅነት እራዕይ ሰጥቶኝ
ውስጤ እይፈላ እንዴት ያስችለኝ
በዚህ ደስ ብሎኝ ብሰብክ ባወራ
መንገድ ዘጋብኝ ያባላጋራ
በአጭር ቀጨሁት ብሎ ሲዝናና
ጥሼው መሄዴን አላየምና
ተጥዬ የምቀር መስሎታልና
እንዲህ የዋዛ መቼ ሆንኩና
መስሎት የፈራሁ ገና ለገና
ጉዱ ፈላበት ነካካኝና
አዝማች · Chorus
ወረደ አምላኬ ከሃያላን ጋራ
ከሰማይ መቅደሱ አያበራ
ወረደ አምላኬ ከሃያላኑ ጋር
በሰልፉ ስለ እኔ ሊዋጋ
አልመለስም ሰልፉን ፈርቼ ፤ አልመለስም ቅባቱን ይዤ
አልመለሰም አምላኬን ይዤ ፣ አልመለስም ቅባቱን ይዤ
አልመለስም ሰልፉን ፈርቼ ፤ አልመለስም ቅባቱን ይዤ
ቁጥር 2 · Verse 2
ምንም ቢያወራ እኔ ላልፈራ
አታመልጠኝም ቢል ለፉከራ
ዛቻ ፉከራ ላይሆን ላይሰራ
ጸጉሬን ዐይነካም ምን ቢንጠራራ
ዝምበል ጠላቴ እስኪ አትፎክር
ከአንተ የሚበልጥ አለኝ እግዚአብሔር
ሰልፉ የእግዚአብሔር መሆኑን ሳያውቅ
ዘሎ ገባበት አቤት መናናቅ
ወይ አለማሰብ አዬ መሳሳት
መቼ ይሆናል በእሳት መጫወት
አዝማች · Chorus
ወረደ አምላኬ ከሃያላን ጋራ
ከሰማይ መቅደሱ አያበራ
ወረደ አምላኬ ከሃያላኑ ጋር
በሰልፉ ስለ እኔ ሊዋጋ
አልመለስም ሰልፉን ፈርቼ ፤ አልመለስም ቅባቱን ይዤ
አልመለሰም አምላኬን ይዤ ፣ አልመለስም ቅባቱን ይዤ
አልመለስም ሰልፉን ፈርቼ ፤ አልመለስም ቅባቱን ይዤ
ቁጥር 3 · Verse 3
ጠላቴ ሲያየኝ መስሎት ማልበቃ
ጌታ ግን ቀባኝ አድርጐ አለቃ
ሰው ሁሉ ሲያየኝ አንተ ብላቴና
አትችለውም ህጻን ነህና
ህጻን ብመስልም ምንም ማልረባ
ገልብጬው መጣሁ ያንን ገለባ
ሲያስብ ጠላቴ በአምላኬ ማፍር
እኔ ሳለቅስ እርሱ ሊፎክር
ተአምር ሰራና የእኔ እግዚአብሔር
ከዐይኔ አስወገደው እስኪ ልዘምር
አዝማች · Chorus
ወረደ አምላኬ ከሃያላን ጋራ
ከሰማይ መቅደሱ አያበራ
ወረደ አምላኬ ከሃያላኑ ጋር
በሰልፉ ስለ እኔ ሊዋጋ
አልመለስም ሰልፉን ፈርቼ ፤ አልመለስም ቅባቱን ይዤ
አልመለሰም አምላኬን ይዤ ፣ አልመለስም ቅባቱን ይዤ
አልመለስም ሰልፉን ፈርቼ ፤ አልመለስም ቅባቱን ይዤ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ