Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ይመለካል ገና

Yemelekal Gena

ትራክ 8 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ለአምላኬ ዝማሬ ለጌታ ምስጋና

ገና እዘምራለሁ ገና እንደገና (፪x)

ገና እንደገና (እንደገና) (፰x)

ለመጀመሪያማ ሁሉም ይንቀዋል

እየዋለ ሲያድር ጉዱ ይገለጣል

የናቀው ተንቆ ከእግሩ ስር ሲወድቅ

ጌታ እንደዚህ ነው ሁሉን ሲያንበረክክ

እንዲህ አልነበርኩኝም እኔ (፫)

ለውጦኝ አየሁ መድህኔ (፪)

አምላኬ ያደረገው ለእኔ

አያልቅም ቢወራ ሁሌ (፭x)

ገና መች ተጀመረና

ይነገራል ይሰበካል ገና

ጌታ የኔ ገናና

ገና ይመለካል ገና (፪x)

ይመለካል ገና ፣ ይመለካል ገና (፬x)

ለአምላኬ ዝማሬ ለጌታ ምስጋና

ገና እዘምራለሁ ገና እንደገና (፪x)

ገና እንደገና (እንደገና) (፰x)

ውዳሴና ክብር ይሁንለት ላውራ

በመስቀሉ ስራ ህይወቴን ለሰራ

ለጨነቀው ደራሽ ልዩ አምላክ ነውና

ለዚህ ለኢየሱሴ ይድረሰው ምስጋና

እንዲህ አልነበርኩኝም እኔ (፫)

ለውጦኝ አየሁ መድህኔ (፪)

አምላኬ ያደረገው ለእኔ

አያልቅም ቢወራ ሁሌ (፭x)

ገና መች ተጀመረና

ይነገራል ይሰበካል ገና

ጌታ የኔ ገናና

ገና ይመለካል ገና (፪x)

ይመለካል ገና ፣ ይመለካል ገና (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ