ይቅርብን
Yeqreben
ትራክ 6 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ኀጢአት መሆኑን እየተረዳን በደምብ አውቀነው
የምንአለበት ተዉ ባክህን ብለን አለፍነው
በስግ ስሜት እየተነዳን ስንሸፋፍነው
ያወቅነው መስሎን እንዲያው በመላ የዘመኑ ሰው
በሰንበት ብቻ ስንንመላለስ ልማድ ሆኖብን
አይፈሪሳዊ እያለ ጌታ ግብዞች ሲለን
እንደ መቃብር ከላይ ስንታይ ኖራ ተቀብተን
ቅሚያና ዝርፊያ ውስጣችን ሞልቷል በመንፈስ ላየን
አዝማች · Chorus
ይቅርብን እንተው ፣ ይቅርብን እንተው
ለእኛ ሚሆነው ጌታ ብቻ ነው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ትንኝ አጥርተው ግመል እየዋጡ ቢመላለርሱ
የበግ ለምድ ለብሰው ለታይታ ብቻ ጻድቅ ቢመስሉም
ጌታ ይመጣል በእጁ መርሽ ይዞ ቤቱን ሊያጠራ
ዝም ብሎ አያይም በመቅደሱ ውስጥ ኀጢአት ሲደራ
ስንዴና እንክርዳድ ጐተራ አይገባም ብደምብ ሳይጠራ
ከመንጋው መሃል ቢመሳሰሉ ሆኖ በጋራ
ጌታ ሳይለው ይህ ክርስቲያን ነው ሰው ሁሉ ቢለው
መጋፋት አይደል የእርሱ መለኪያው ጌታን መኖር ነው
አዝማች · Chorus
ይቅርብን እንተው ፣ ይቅርብን እንተው
ለእኛ ሚሆነው ጌታ ብቻ ነው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ምንም ቢማሩ ለውጥ ከሌለ መምህር ቢባሉ
አያስደንቅም ወረቀት ይዘው ዲግሪ ቢጭኑ
አንቱ ቢባሉ ለምን ይጠቅማል ሕይወት ከሌለው
ዝናና ክብር በምድር ያለው ሁሉም ጠፊ ነው
እንዲያው በጭፍር ምንም ሳይገባው የጌታ አላማው
ቢሰብክ ቢዘምር ቃሉን አጣፍጦ ወደድኩህ ቢለው
ለራሱ ክብር እያመቻቸ የኖረውን ሰው
ተጠቀመብኝ አለ እንጂ እራሱ ጌታ መች አለ
አዝማች · Chorus
ይቅርብን እንተው ፣ ይቅርብን እንተው
ለእኛ ሚሆነው ጌታ ብቻ ነው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ