Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ምህረትህ በዛ ለእኔ

Mehereteh Beza Lenie

ትራክ 7 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አስፈራርተህ ሳይሆን እኔን የጠራኸኝ

በሃይልም አይደለም ወይ አልጠመዘዝከኝ

ቸርነትህ በዝቶ ምህረትህ ሳበኝ (፪x)

ቸርነትህ በዝቶ ጌታዬ ፍቅርህ ነው የሳበኝ አምላኬ

ክበር ክበር (፬x) በሰማይ በምድር አንተ የኔ እግዚአብሄር

ክበር ክበር (፬x) በሰማይ በምድር አንተ የኔ እግዚአብሄር

በችርነትህ በምህረትህ ዛሬም ቆምያለሁ ይኽው በቤትህ (፪x)

አንተ ነህ አምላኬ የምለው ጌታዬ

በሰው ልክ ያልሆነው ምህረትህ በዛ ለኔ (፭x)

እኔው እራሴ እንጂ አንተ አላስገደድከኝ

ስትሰራ አየሁና ቃልህ ቢማርከኝ

እርም ካንተ ሌላ አልኩኝ ስትመችኝ (፪x)

እርም ካንተ ሌላ ብያለሁ ቃልህ ሲማርከኝ ምያለሁ

በችርነትህ በምህረትህ ዛሬም ቆምያለሁ ይኽው በቤትህ (፪x)

አንተ ነህ አምላኬ የምለው ጌታዬ

በሰው ልክ ያልሆነው ምህረትህ በዛ ለኔ (፭x)

ክበር ክበር (፬x) በሰማይ በምድር አንተ የኔ እግዚአብሄር

ክበር ክበር (፬x) በሰማይ በምድር አንተ የኔ እግዚአብሄር

አለም ሳይፈጠር ኑሮዬን አስወገድከው

በገዛ ፈቃዴ ህይወቴን ወሰንከው

አለም ከሚገዛኝ ክብሬ ላንተ ይኽው (፫x)

አለም ከሚገዛኝ ኢየሱሴ በአንተ ነው የሚያምረው ጌታዬ

በችርነትህ በምህረትህ ዛሬም ቆምያለሁ ይኽው በቤትህ (፪x)

አንተ ነህ አምላኬ የምለው ጌታዬ

በሰው ልክ ያልሆነው ምህረትህ በዛ ለኔ (፭x)

አንተ ነህ አምላኬ የምለው ጌታዬ

በሰው ልክ ያልሆነው ምህረትህ በዛ ለኔ (፭x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ