በእርሱ ተለወጥኩኝ
Bersu Telewetkugn
2000 · ትራክ 3 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በእርሱ ተለወጥኩኝ እንደሌላ ሰው ሆንኩኝ (፪x)
ውስጤ ኢየሱስ ገባ ፈካሁ እንደ አበባ
ባለውለታዬ ይባረክ ጌታዬ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ቀድሞ እንደምኖረው የሞት ኑሮ አልኖርም
ኃጢአት ለመቃረም ወደ ዓለም አልወርድም
ጥፋት አያምረኝም መንፈሱ ገዝቶኛል
ቅዱስ ደሙን ረጭቶብኝ ቅዱስ አድርጐኛል
አዝማች · Chorus
በእርሱ ተለወጥኩኝ እንደሌላ ሰው ሆንኩኝ (፪x)
ውስጤ ኢየሱስ ገባ ፈካሁ እንደ አበባ
ባለውለታዬ ይባረክ ጌታዬ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሁሉን እርግፍ አድርጌ ጠቀመኝ መምጣቴ
ውዴ አላሳፈረኝም ሆነኝ እረዳቴ
አሁን አያይም ዓይኔ ወደ ሥጋ ለባሽ
የሰው እጅ አላይም አግኝቻለሁ አጉራሽ
አዝማች · Chorus
በእርሱ ተለወጥኩኝ እንደሌላ ሰው ሆንኩኝ (፪x)
ውስጤ ኢየሱስ ገባ ፈካሁ እንደ አበባ
ባለውለታዬ ይባረክ ጌታዬ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ጩኸቴን ይሰማል ድምጼ ይናፍቀዋል
አሸናፊው አምላኬ ድል አስለምዶኛል
እምበረከካለሁ ዛሬም በጸጋው ዙፋን ስር
ሲቀበር አያለሁ የተጋባኝ ችግር
አዝማች · Chorus
በእርሱ ተለወጥኩኝ እንደሌላ ሰው ሆንኩኝ (፪x)
ውስጤ ኢየሱስ ገባ ፈካሁ እንደ አበባ
ባለውለታዬ ይባረክ ጌታዬ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
የገዛኝ ተገዛልኝ አዛዡ ሆኛለሁ
ባለማዕረግ ሆንኩኝ ስልጣን አግኝቻለሁ
የመድሃኒቴን ስም ስጠራ መደንገጥ
ልማድ አድርጐታል ዲያቢሎስ መፈርጠጥ
አዝማች · Chorus
በእርሱ ተለወጥኩኝ እንደሌላ ሰው ሆንኩኝ (፪x)
ውስጤ ኢየሱስ ገባ ፈካሁ እንደ አበባ
ባለውለታዬ ይባረክ ጌታዬ (፫x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ባለዉለታዬ ይባረክ ጌታዬ (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ