ታሪኬ ተለውጧል
Tarikie Telewetual
2000 · ትራክ 11 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ታሪኬ ተለውጧል ሌላ ሰው ሆኛለሁ
እውነተኛውን አዳኝ አግኝቼ አርፌያለሁ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
መረጠኝ ሳልመርጠው ፈለገኝ ሳልፈልገው
ከዜምናት በፊት ያሰበውን አደረገው
ማን ሊከለክለው ነው ኧረ ማን ሊቃወመው
ኃጢአተኛውን ወዶት በደሙ ከቀደሰው
አዝማች · Chorus
ታሪኬ ተለውጧል ሌላ ሰው ሆኛለሁ
እውነተኛውን አዳኝ አግኝቼ አርፌያለሁ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የሞት መውጊያው ተሰብሮ ስልጣን አጣ በእኔ ላይ
አልቻለም ሊያስቀረኝ ከመንግሥተ ሰማይ
አልመለስባትም ወደ እዚያች መራራ ዓለም
ከእንግዲህ የኢየሱስ ነኝ እስከ ዘለዓለም
አዝማች · Chorus
ታሪኬ ተለውጧል ሌላ ሰው ሆኛለሁ
እውነተኛውን አዳኝ አግኝቼ አርፌያለሁ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ሳላውቀው ያሰረኝን የገዛኝን ረገጥኩት
ክፉ ባለጋራዬን አለሁ እየተበቀልኩት
ኃይል አለው መንፈስ አለኝ ባዶዬን አይደለሁም
ደፍሬው እዋጋዋለሁኝ ጠላቴን አልሸሸውም
አዝማች · Chorus
ታሪኬ ተለውጧል ሌላ ሰው ሆኛለሁ
እውነተኛውን አዳኝ አግኝቼ አርፌያለሁ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ለክፋት የፈጠኑት እግሮቼ ዛሬ ሰክነው
ማዳኑን ለመናገር ለወንጌል እየሮጡ ነው
የታሰሩ እንዲፈቱ እንደ እኔ እንዲለቀቁ
ከጨለማ ዓለም ወጥተው እንደ ፀሐይ እንዲደምቁ
አዝማች · Chorus
ታሪኬ ተለውጧል ሌላ ሰው ሆኛለሁ
እውነተኛውን አዳኝ አግኝቼ አርፌያለሁ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ