ሰው ታደርጋለህ
Sew Tadergaleh
2000 · ትራክ 2 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ከጢሻ ከማጥ ውስጥ አውጥተህ
ቁጥር 1 · Verse 1
በከበረ ስፍራ ላይ ታስቀምጣለህ
ሰው ታደርጋለህ (ጌታ) እንዴት መልካም ነህ
ሰው ታደርጋለህ እንዴት መልካም ነህ (ኢየሱስ)
ሰው ታደርጋለህ እንዴት መልካም ነህ (፪x)
እንደ እኔ አይነቱን ክፉ ሰው
ከኃጢአተኞች ሁሉ የባሰው
እንዴት አሰብከኝ መረጥከኝ
ምኔን አይተህ ነው የወደድከኝ
የፍቅርህን ልክ ለመግለጽ ጌታዬ ቋንቋ የለኝም
ከስግደት ከአምልኮ ሌላ የምሰጥህ እኔ ሌላ አላገኝም
አዝማች · Chorus
ከጢሻ ከማጥ ውስጥ አውጥተህ
ቁጥር 2 · Verse 2
በከበረ ስፍራ ላይ ታስቀምጣለህ
ሰው ታደርጋለህ (ጌታ) እንዴት መልካም ነህ
ሰው ታደርጋለህ እንዴት መልካም ነህ (ኢየሱስ)
ሰው ታደርጋለህ እንዴት መልካም ነህ (፪x)
እናት አባት ሆነኀኛል እውነተኛ ወላጅ ሆንከኝ
እያበላህ እያጠጣህ በእቅፍህ ላይ አሳደከኝ
ውለታህ ዝም አያሰኝም የደስታ እምባ ያመጣል
ያ ብዙ ቸርነትህ ቢወራ መቼ ያልቃል
አዝማች · Chorus
ከጢሻ ከማጥ ውስጥ አውጥተህ
ቁጥር 3 · Verse 3
በከበረ ስፍራ ላይ ታስቀምጣለህ
ሰው ታደርጋለህ (ጌታ) እንዴት መልካም ነህ
ሰው ታደርጋለህ እንዴት መልካም ነህ (ኢየሱስ)
ሰው ታደርጋለህ እንዴት መልካም ነህ (፪x)
እኔን ከድጥ ላይ ለማንሳት ከማንም ጋር አልተማከርክ
ልጄ ነው ወልጄሃለሁ ለማለትም በእኔ አላፈርክ
በድኔን አፈር ልታለብስ ኑሮዬ እንዲሆን ምድር ሥር
ትንሳኤ ልትሰጠኝ እንጂ አልመጣህ እኔን ልትቀብር
አዝማች · Chorus
ከጢሻ ከማጥ ውስጥ አውጥተህ
ቁጥር 4 · Verse 4
በከበረ ስፍራ ላይ ታስቀምጣለህ
ሰው ታደርጋለህ (ጌታ) እንዴት መልካም ነህ
ሰው ታደርጋለህ እንዴት መልካም ነህ (ኢየሱስ)
ሰው ታደርጋለህ እንዴት መልካም ነህ (፪x)
ያለ መታሰቢያ እንዳልቀር ሲኦል እንዳልወረወር
የሰይጣን መጫወቻ እንዳልሆን እንዳልፈጅብህ በእቶን
በሕይወት መዝገብ ላይ ስሜን በከበረው ደምህ ጻፍከው
አቤት የተረሳውን ሰው ደግመህ ወልደህ ሰው አደረከው
አዝማች · Chorus
ከጢሻ ከማጥ ውስጥ አውጥተህ
ቁጥር 5 · Verse 5
በከበረ ስፍራ ላይ ታስቀምጣለህ (ጌታ)
ሰው ታደርጋለህ እንዴት መልካም ነህ
ሰው ታደርጋለህ እንዴት መልካም ነህ (ኢየሱስ)
ሰው ታደርጋለህ እንዴት መልካም ነህ (፪x)
ሰው ታደርጋለህ (ጌታ) እንዴት መልካም ነህ (ኢየሱስ)
ሰው ታደርጋለህ እንዴት መልካም ነህ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ