ተገልብጧል ታሪክ
Tegelbetual Tarik
2000 · ትራክ 6 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ተገልብጧል ታሪክ ሌላ ነገር ተፈጥሯል
ንጉሡ እግዚአብሔር ምስኪኑን እረድቶታል
ተዓምር ነው ድንቅ ነው ይሄ ሰው ቆመ በእግሩ
ተወራ በምድር ላይ በአምላኩ እርሱ መክበሩ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ይሄው ተራ ደርሶት ምሥጋናን ሊሰዋለት
ወጣ አደባባይ ላይ ማቁ ተቀዳዶለት
አከናውኖለታል ደስታው ወሰን ልክ የለው
ይሄን ችግረኛ እግዚአብሔር አሰበው
አዝማች · Chorus
ተገልብጧል ታሪክ ሌላ ነገር ተፈጥሯል
ንጉሡ እግዚአብሔር ምስኪኑን እረድቶታል
ተዓምር ነው ድንቅ ነው ይሄ ሰው ቆመ በእግሩ
ተወራ በምድር ላይ በአምላኩ እርሱ መክበሩ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ተባርኮለት ጓዳው መከራውን እረሳው
ታምኖበታልና ጌታው በብዙ እረዳው
ምርኮው ተመለሰ የአጥፍ እጥፍ ሆነለት
ካሰው ያጣውን ሁሉ እየነዳ አመጣለት
አዝማች · Chorus
ተገልብጧል ታሪክ ሌላ ነገር ተፈጥሯል
ንጉሡ እግዚአብሔር ምስኪኑን እረድቶታል
ተዓምር ነው ድንቅ ነው ይሄ ሰው ቆመ በእግሩ
ተወራ በምድር ላይ በአምላኩ እርሱ መክበሩ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ተራራ ላይ አወጣው የናቁት ሁሉ እንዲያዩት
በምላስ አለንጋ ሌት ተቀን የገረፉት
ሲሸላልመው አዪ በሞገስ ሲቀባባው
ውስጡንም ላዩንም እንደ አበባ ሲያፈካው
አዝማች · Chorus
ተገልብጧል ታሪክ ሌላ ነገር ተፈጥሯል
ንጉሡ እግዚአብሔር ምስኪኑን እረድቶታል
ተዓምር ነው ድንቅ ነው ይሄ ሰው ቆመ በእግሩ
ተወራ በምድር ላይ በአምላኩ እርሱ መክበሩ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ቀና አለ ከአንገቱ ማቀርቀሩ ቀረና
ያስተከዘው ኑሮ ድንገት ተቀየረና
እነዛም ዘባቾች ሲረቱ አሉ ተደንቀው
የረዳህን አምላክ እርሱን ነው የምናመልከው
አዝማች · Chorus
ተገልብጧል ታሪክ ሌላ ነገር ተፈጥሯል
ንጉሡ እግዚአብሔር ምስኪኑን እረድቶታል
ተዓምር ነው ድንቅ ነው ይሄ ሰው ቆመ በእግሩ
ተወራ በምድር ላይ በአምላኩ እርሱ መክበሩ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ተአምር ነው ድንቅ ነው ይሄ ሰው ቆመ በእግሩ
ተወራ በምድር ላይ በአምላኩ እርሱ መክበሩ (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ