ይመጣል
Yemetal
2000 · ትራክ 5 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ይመጣል ፣ መልስ ይዞ ይመጣል
ቀን ቀጥሯል ይመጣል ፣ ኑሮን ያጣፍጣል (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ሀዘንን በደስታ ዋይታንም በሆታ
ከስቃይ ገላግሎ ሊሞላ በእፎይታ
ታምራቱን ሊያደርግ እጅን በአፍ ላይ ሊያስጭን
ሊያስብ ምስኪኖችን
አዝማች · Chorus
ይመጣል ፣ መልስ ይዞ ይመጣል
ቀን ቀጥሯል ይመጣል ፣ ኑሮን ያጣፍጣል (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ልጆቹን ሊያጽናና ሮሮዋቸውን ሊያርቅ
ችግርን ሊመታ ከጭንቀት ሊያላቅቅ
ለጠበቁት ጸንተው እርሱን እርሱን ላሉት
ሲባረኩ ያያሉ
አዝማች · Chorus
ይመጣል ፣ መልስ ይዞ ይመጣል
ቀን ቀጥሯል ይመጣል ፣ ኑሮን ያጣፍጣል (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ወጀቡን ሊገስጽ አውሎ ንፋሱንም
ገስግሶ ሊመጣ ሳይፈራ ማንንም
የተናጋን ኑሮ ሰላም ሊዘራበት
አቤት ሲችልበት
አዝማች · Chorus
ይመጣል ፣ መልስ ይዞ ይመጣል
ቀን ቀጥሯል ይመጣል ፣ ኑሮን ያጣፍጣል (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
መከራም ነገ ያልፋል ችግርም ይረሳል
የሚያጠግብ እንጀራ በአባት እጁ ያጐርሳል
በተትረፈረፈ ፣ በሚበቃ ኑሮ
ያኖራል አክብሮ
አዝማች · Chorus
ይመጣል ፣ መልስ ይዞ ይመጣል
ቀን ቀጥሯል ይመጣል ፣ ኑሮን ያጣፍጣል (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
እስከመቼ ድረስ እናዝናለን ላሉ
ተዋረድን አጣን ተናቅን ከሰው ሁሉ
ተስፋ ለቆረጡ መልካም ዜና አለው
ይላል ደርሻለሁ
አዝማች · Chorus
ይመጣል ፣ መልስ ይዞ ይመጣል
ቀን ቀጥሯል ይመጣል ፣ ኑሮን ያጣፍጣል (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ