ኢየሱስ የዋሁ
Eyesus Yewahu
2000 · ትራክ 10 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ኢየሱሴዋ ትሁቱ ወዳጄ
ጠበቃዬ ብቸኛ አማላጄ (ብቸኛ አማላጄ)
ቁጥር 1 · Verse 1
ከዘለዓለም ቁጣ ከሲዖል አዳንከኝ
እኔ ኃጢያተኛውን ኧረ እንዴት ወደድከኝ (፪x)
በቅጣት አለንጋ ብዙ ተገረፍኩኝ
በገዛ ጥፋቴ ተጠቃሁ ቆሰልኩኝ
እየተንገዳገድኩ አመጻዬ አስክሮኝ
ገደል ከቶኝ ነበር ባትይዘኝ ገፍትሮኝ
አዝማች · Chorus
ኢየሱሴዋ ትሁቱ ወዳጄ
ጠበቃዬ ብቸኛ አማላጄ (ብቸኛ አማላጄ)
ቁጥር 2 · Verse 2
ከዘለዓለም ቁጣ ከሲኦል አዳንከኝ
እኔ ኃጢያተኛውን ኧረ እንዴት ወደድከኝ
የተፈጠርኩበት ምክንያቱ ገብቶኛል
የመዳኔ ሚስጥር ተገልጦልኛል
የአንተን አባትነት የልጅነቴን መብት
በነጻ አገኘሁት የዘላለሙን ሀብት
አዝማች · Chorus
ኢየሱሴዋ ትሁቱ ወዳጄ
ጠበቃዬ ብቸኛ አማላጄ (ብቸኛ አማላጄ)
ቁጥር 3 · Verse 3
ከዘለዓለም ቁጣ ከሲኦል አዳንከኝ
እኔ ኃጢያተኛውን ኧረ እንዴት ወደድከኝ
ተታልዬ ኖርኩኝ ማንነቴ አባብሎኝ
የመርጥኩት መንገድ የሚያዋጣኝ መስሎኝ
ጊዜያዊው እርካታ ዓለም የምትሰጠው
ላዩ ቢጣፍጥም ውስጡ ግን መርዝ አለው
አዝማች · Chorus
ኢየሱሴዋ ትሁቱ ወዳጄ
ጠበቃዬ ብቸኛ አማላጄ (ብቸኛ አማላጄ)
ቁጥር 4 · Verse 4
ከዘለዓለም ቁጣ ከሲኦል አዳንከኝ
እኔ ኃጢያተኛውን ኧረ እንዴት ወደድከኝ
እኔ የአለኝን አጥቶ ለሚንከራተተው
ጽድቅ የኖረው መስሎት ለሚመጻደቀው
የውስጥ አይኑ በርቶ ምነው እውነቱን ባየ
ለክፋቱ ስትል እንደተሰቃየህ
አዝማች · Chorus
ኢየሱሴዋ ትሁቱ ወዳጄ
ጠበቃዬ ብቸኛ አማላጄ (ብቸኛ አማላጄ)
ቁጥር 5 · Verse 5
ከዘለዓለም ቁጣ ከሲኦል አዳንከኝ
እኔ ኃጢያተኛውን ኧረ እንዴት ወደድከኝ (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ