Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ጌታ ነው

Geita New

2000 · ትራክ 9 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አለኝ ያልኩት ሁሉ በንፋስ ሲወሰድ

ከመከራው ብዛት ብቻዬን ስሰደድ

ተስፋዬ ተሟጦ ምድረ በዳ ሳለሁ

እጁን የዘረጋ እንግዳ ሰው አየሁኝ

ጌታ ነው ኢየሱስ ነው

ለእኔ የደረሰው (፪x)

ቀንበር የከበደኝ ሸግም የበዛብኝ

ያየኝ ሁሉ የጠላኝ ወዳጅ የራቀብኝ

ተረስቼ ማንም የት ደረሰ አይለኝ

አንድ ድምጽ ሰማሁ ና ልጄ የሚለኝ

ጌታ ነው ኢየሱስ ነው

ለእኔ የደረሰው (፪x)

የኀጢአት ባሪያ ሆኜ ደስታ ከእኔ ርቆ

ከጭንቀቴ ብዛት እኔነቴ አልቆ

ሌት ተቀን ፍራቻ ኑሮ ሆኖ እሮሮ

ሞቶ ወስዶኝ ነበር ኢየሱስ ባይደርስ ኖሮ

ጌታ ነው ኢየሱስ ነው

ለእኔ የደረሰው (፪x)

ባወራው ባወራው አያልቅም ብናገር

እንዴት እንዳወጣኝ ከዚያ ከሞት አገር

እድሜ ቀጥሎልኝ እስካሁን አቆየኝ

ሲዖል ቤቴ ነበር አምላኬ ባያየኝ

ጌታ ነው ኢየሱስ ነው

ለእኔ የደረሰው (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ