ልብ ለልብ ተከባብዶ
Leb Leleb Tekebabdo
2000 · ትራክ 7 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ልብ ለልብ ተከባብደን እንዴት ይኖራል
ያለ ፍቅር ክርስትና ምን ይረባናል
እወድሃለሁ/እወድሻለሁ እያሉ መሸነጋገል
ከንቱ ነው ሰው እየጠሉ ጌታን ማገልገል (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
በአንድ ልብ አብሮ መኖርን እንለማመድ
መከፋፈሉ ይበቃናል ተዉ እንዋደድ
መራራቁም እየሰፋ እንዳንለያይ
እንሰባሰብ እናምልክ ጌታን በአንድ ላይ
አዝማች · Chorus
ልብ ለልብ ተከባብደን እንዴት ይኖራል
ያለ ፍቅር ክርስትና ምን ይረባናል
እወድሃለሁ/እወድሻለሁ እያሉ መሸነጋገል
ከንቱ ነው ሰው እየጠሉ ጌታን ማገልገል (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በቤት ሌላ ውጪ ሌላ ሁለት ዐይነት ሰው
ችላ እያልን ትዕዛዛቱን እየረሳነው
ሁሌ ወተት እየተጋትን እየጫጨን ነው
ዛሬ እንወስን እንለወጥ ለእርሱ እንመቸው
አዝማች · Chorus
ልብ ለልብ ተከባብደን እንዴት ይኖራል
ያለ ፍቅር ክርስትና ምን ይረባናል
እወድሃለሁ/እወድሻለሁ እያሉ መሸነጋገል
ከንቱ ነው ሰው እየጠሉ ጌታን ማገልገል (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ሲቀርቡ ሳቅ ሲርቁ ሃሜት ልማድ አድርገነው
ጌታ እንዳያልፍ እንዳይሰራ እጁን ይዘነው
ከአንገት በላይ ወድሃለሁ ይህም አለማድላት
እውነተኛይቱን ፍቅር ወዴት አደረግናት
አዝማች · Chorus
ልብ ለልብ ተከባብደን እንዴት ይኖራል
ያለ ፍቅር ክርስትና ምን ይረባናል
እወድሃለሁ/እወድሻለሁ እያሉ መሸነጋገል
ከንቱ ነው ሰው እየጠሉ ጌታን ማገልገል (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
በቃል ብቻ አኗደድ ተግባር ይጨመር
ፍቅራችንን ሁሉ እንዲያውቀው እያደር ይመር
እጅ ለእጅ እንያያዝ ስራም እንስራ
ጠላት መግቢያ ቀዳዳ አያግኝ እኛን ሲያይ ይፍራ
አዝማች · Chorus
ልብ ለልብ ተከባብደን እንዴት ይኖራል
ያለ ፍቅር ክርስትና ምን ይረባናል
እወድሃለሁ/እወድሻለሁ እያሉ መሸነጋገል
ከንቱ ነው ሰው እየጠሉ ጌታን ማገልገል (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ