ለችግረኞች አሁን እነሳለሁ
Lechegeregnoch Ahun Enesalehu
2000 · ትራክ 1 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
"ስለ ድሆች መከራ ስለ ችግረኞችም ጩኀት
እግዚአብሔር አሁን እነሳለሁ ይላል
መድሃኒት አደርጋለሁ በላይ በላይ እገልጣለሁ"
አዝማች · Chorus
ለችግረኞች አሁን እነሳለሁ
ማዳኔን ይዤ እገለጣለሁ
የበረታውን ክንዴን ያያሉ
በብዙ ብዙ ይባረካሉ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ተስፋ የሚያደርጉት የሚረዳቸው
ከእኔ በስተቀር ማንም የላቸው
. (1) . ተሞልተው ጠርተዉኛል
ቶሎ ድረስልን ብለውኛል
ያለቀሱትን ለቅሶ አይቻለሁ
ጸሎታቸውን ሰምቼዋለሁ
ከእንግዲህ ላይራቡ ልጆቼ
ጥላ ባመጡላቸው እጆቼ
አዝማች · Chorus
ለችግረኞች አሁን እነሳለሁ
ማዳኔን ይዤ እገለጣለሁ
የበረታውን ክንዴን ያያሉ
በብዙ ብዙ ይባረካሉ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
መከራው በዝቶ ብዙ ተማረው
ያለ ልክ አጥተው ተቸግረው
ሞትን ሲመርጡ ከመኖር ይልቅ
ያላቸው ሁሉ ተሟጦ ሲያልቅ
በከንቱ ሲጨነቁ አየኋቸው
እኔን የሚያክል ጌታ እያላቸው
ስቃያቸውን አንጀቴ አልቻለም
በቃ ብያለሁ ከእንግዲህ ሃዘን የለም
አዝማች · Chorus
ለችግረኞች አሁን እነሳለሁ
ማዳኔን ይዤ እገለጣለሁ
የበረታውን ክንዴን ያያሉ
በብዙ ብዙ ይባረካሉ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ሁሉ እቋቸው ብቸኛ ሆነው
የሚደርስልን ኧረ ማነው
ወዳች ዘመዶቻቸው ሸሿቸው
አናውቃችሁም ብለው ካዷቸው
ያጥላሏቸውን አሳፍራለው
እንደተናቁ መች አስቀራለው
ወዮ ባሉበት አንደበታቸው
ሰው ሁሉ ያያል ሳዘምራቸው
አዝማች · Chorus
ለችግረኞች አሁን እነሳለሁ
ማዳኔን ይዤ እገለጣለሁ
የበረታውን ክንዴን ያያሉ
በብዙ ብዙ ይባረካሉ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
እንጀራ ለአጡ መጋቢያቸው ነኝ
ለተጠሙ ሁሉ የሚጠታ አለኝ
ወዴኔ መጥተው ከቶ አያፍሩም
የለመኑኝን አንዳች አያጡም
ለጠሩኝ ሁሉ ባለጠጋ ነኝ
የምስኪኖችን እምባ አባሽ ነኝ
ሁሉን ሸለቆን መሙላት አውቃለሁ
ችግረኞችን እባርካለው
አዝማች · Chorus
ለችግረኞች አሁን እነሳለሁ
ማዳኔን ይዤ እገለጣለሁ
የበረታውን ክንዴን ያያሉ
በብዙ ብዙ ይባረካሉ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ