ከአንተ በላይ
Kante Belay
2000 · ትራክ 8 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሰማይ ሆነ ምድር ጌታ ሆኖ የሚመለከው
ስግደት የተገባው . (1) . ያለኸው
ዓይናችን በራልን ማን አዳኝ እንደሆነ አየን
ስምህ ክብራችን ነው የአንተ ነን አንኮራለን
እውነተኛው አምላክ ለህዝቦችህ ያለህ
አዝማች · Chorus
ከአንተ በላይ አምላክ የለም ከአንተ በላይ (፰x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ስንቱን ደፋርና ትዕቢተኛን ጥለሃል
በውጊያ ሜዳ ላይ ቁጣህም ታይቶልሃል
ሞኛሞኞች ሆነው ሊጣሉህ መጡ ታጥቀው
የውርደት አቧራ ከደናቸው . (2) .
ጀግና ነው አርሱ አሉ . (3) . ጌታቸው
አዝማች · Chorus
ከአንተ በላይ ጀግና የለም ከአንተ በላይ (፰x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ወልደህ እንደሰው ምድረ በዳ ላይ አትጥልም
እንጀራም እያለ ድንጋይ ብላ አትልም
የወላጅ አንጀትህ ይንሰፈሰፍልናል
ብሩካን እጆችህ ቆርሰው ይመግቡናል
እንደአንተ ያለ አባት የትስ ይገኝልናል
አዝማች · Chorus
ከአንተ በላይ አባት የለም ከአንተ በላይ (፰x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ለበሽታ ሁሉ ፍቱን መድሃኒት አለህ
ሞት አፋፍ ላይ ላሉ ብቸኛ መልስ አንተ ነህ
በእጆችህ ተዳሰው አፎይ ያሉ ብዙ አሉ
ሌት ተቀን ከማልቀስ ክእንባ የተገላገሉ
ይኸው ተፈውሰው ለክብርህ ይዘምራሉ
አዝማች · Chorus
ከአንተ በላይ ፈዋሽ የለም ከአንተ በላይ (፰x)
ቁጥር 5 · Verse 5
"ሃሌሉያ በሰማይ በምድር ቢሆን
እንደ አንተ ያለ ማንም የለም ጌታ ሆይ
ከምድር ጫፍ እስከምድር ጫፍ
ታላቁ ሥምህ የተባረከ ይሁን"
ሃሌሉያ(፲፮x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ