Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

በየማለዳው

Beyemaledaw

2007 · ትራክ 12 · 5:47 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ስለ ዛሬ ምን ታውቂያለሽ ቢሉኝ

አንድ ነገር አንድ መልስ አለኝ

በእውነት በእርግጠኛነት

አለ የእግዚአብሔር ቸርነት

ስለ ነገስ ምን ታውቂያለሽ ቢሉኝ

አንድ ነገር አንድ ዕውቀት አለኝ

በእውነት በእርግጠኛነት

አለ የእግዚአብሔር ቸርነት

በየማለዳው የምረዳው

ዕለት በዕለት ሚታይ እውነት (፪x)

እንደ እግዚአብሔር ያለ እንደ ሌለ

እግዚአብሔር ቸር እንደሆነ (፪x)

ቸር ባይሆን ባለ ምህረት

እኔ/አንዷ ነበርኩ ከሚጠፉት (፪x)

ለክፉዎችም ቸር ለማያመሰግኑት

ለሚወዱትም ቸር ለሚያምኑበት (፪x)

ያለጠፋሁት በምን ምክንያት

ከቦኝ እንጂ የአንተ ምህረት

እያለፈ እየተከተለኝ

ክፉዉን ሁሉ ጥግ አስያዘልኝ

የደረስክለት ያውራ እስኪ ያውራ

ደግነትህን ይመስክር

በአንተ የቀናለት አሃ

የሕይወቱ መስመር (፪x)

ቸር ባትሆን ባለ ምህረት

እኔ/አንዷ ነበርኩ ከሚጠፉት (፪x)

ለክፉዎችም ቸር ለማያመሰግኑህ

ለሚወዱህም ቸር ለሚያምኑብህ (፪x)

አልጣሉኝም ደጋግ እጆችህ

ፍቅር ናቸው ዛሬም ዓይኖችህ

ለዘለዓለም ቤትህ እኖራለሁ

ወደኸኛል እስከ መጨረሻው

የደረስክለት ያውራ እስኪ ያውራ

ደግነትህን ይመስክር

በአንተ የቀናለት አሃ

የሕይወቱ መስመር (፪x)

ቸር ባትሆን ባለ ምህረት

እኔ/አንዷ ነበርኩ ከሚጠፉት (፪x)

ለክፉዎችም ቸር ለማያመሰግኑህ

ለሚወዱትም ቸር ለሚያምኑበህ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ