Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ወዴት አለህ

Wediet Aleh

2007 · ትራክ 6 · 6:08 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ልቤ ዋተተ ዋተተ

መንፈሴም ታወከብኝ

ልጄ አንተን አጥቼ ከጉያዬ

እንዴት ልረፍ በምን anjet chye

እህ እህህህህ

እህህ ሆነብኝ ጠዋት ማታ

ወንድሞችህ ቢኖሩም በቤት

አይተኩትም ለአንተ ያለኝን ቦታ

ወዴት አለህ

ድምጼን ሰምተህ አለሁ በለኛ

ፈጠን ብለህ ወደ እቅፌ ግባ (፪x)

ደጅ/በር አፍ ላይ ቆሞ ያንኳኳል ወዳጅ

ይጣራል ወዳጅ (፪x)

ድምጹን ሲያሰማ አስገባው ከፍተህ

አይጥና ደጅ ፣ አይጥና ደጅ (፪x)

እናት ትረሳ ይሆናል አምጣ የወለደችውን

እኔማ እንዴት እንዴት ነው እንዴት

አንተን ጥሎ መኖር በሞቀ ቤት

ልጄን ካልያዝኩት አልረካ

ክርትት አለ ዓይኔ አንተን ፍለጋ

ወድሃለሁ ልጄ ናና ናና

ሙሉ እንዲሆን የቤቴ ምሥጋና

ወዴት አለህ

ድምጼን ሰምተህ አለሁ በለኛ

ፈጠን ብለህ ወደ እቅፌ ግባ (፪x)

ደጅ/በር አፍ ላይ ቆሞ ያንኳኳል ወዳጅ

ይጣራል ወዳጅ (፪x)

ድምጹን ሲያሰማ አስገባው ከፍተህ

አይጥና ደጅ ፣ አይጥና ደጅ (፪x)

አባ አባባ ስትለኝ

እስቲ ልስማህ ያ ድምጽህ ናፈቀኝ

ሸክምህን አውርድ ከጫንቃህ

ላሳርፍህ አለሁ አባትህ

የሚያሳየው ጐልጐታ

ዛሬም ያው ነው ፍቅሬ መች ተገታ

በላ እንሂድ ወደ ቤታችን

እኔም ልረፍ አግኝቼ አንተን

ወዴት አለህ

ድምጼን ሰምተህ አለሁ በለኛ

ፈጠን ብለህ ወደ እቅፌ ግባ

(ወዴት አለህ) ወዴት አለህ

(ድምጼን ሰምተህ) ድምጼን ሰምተህ

አለሁ በለኛ (አለሁ በለኛ)

ፈጠን ብለህ ወደ እቅፌ ግባ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ