የሰላም ጥጉ
Yeselam Tegu
2007 · ትራክ 11 · 4:49 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ሰው በምን ይረካል ልቡ
ዓለሙም አያልፍም ልኩ
ጌታ ነው የሰላም ጥጉ (፪x)
ኢየሱስ ነው የደስታ ጥጉ
ኢየሱስ ነው የደስታ ጥጉ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ልብህ ሲፈካ እንደ አበባ
በአገኘው ነገር ሲፅናና
ደግሞ በዚያው ልክ የሃዘን ድባብ
ድብት ሲያደርገው ተስፋ ሲቆርጥ
ስንቱ ነው ሚታየው በሕይወት
ለዚያች ዕድሜ ተችሮት
ግን አዋቂ ያ ብልሁ
በአምላክ ሲሆን ነው መደሰቱ
የማይናወጥ ሰላሜን ደስታዬን
እኔ አግኝቻለሁ ኢየሱስ ጌታዬን
የምድር ስኬት ሚሰጠው ምንድን ነው
ከኢየሱስ ሌላ ደስታ አለ ባይ ማን ነው
አዝማች · Chorus
ሰው በምን ይረካል ልቡ
ዓለሙም አያልፍም ልኩ
ጌታ ነው የሰላም ጥጉ (፪x)
ኢየሱስ ነው የደስታ ጥጉ
ኢየሱስ ነው የደስታ ጥጉ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
መች በአንድ ነገር ልብ ይረካል
አንዱ ሲሰጠው ሌላ ይሻል
ያሻውንም ቢያገኝ ሰው ምኞቱ
በቃ አይልም አይሞላለት ቋቱ
ሕይወት የሚረጋው በእረፍት
ኢየሱስ ሲገባ ወደ ቤት
የሰላም ምንጩን ከተጠጉ
ሌላ ደስታ አይፈልጉ
የማይናወጥ ሰላሜን ደስታዬን
እኔ አግኝቻለሁ ኢየሱስ ጌታዬን
የምድር ስኬት ይሰጠው ምንድን ነው
ከኢየሱስ ሌላ ደስታ አለ ባይ ማን ነው (፪x)
አዝማች · Chorus
ሰው በምን ይረካል ልቡ
ዓለሙም አያልፍም ልኩ
ጌታ ነው የሰላም ጥጉ (፪x)
ኢየሱስ ነው የደስታ ጥጉ
ኢየሱስ ነው የደስታ ጥጉ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ