Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ኤልራሂም

Elrahim

2007 · ትራክ 7 · 4:54 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የሹዋ ሮሓሚን

ኤል ሮሓሚን

ሲምር ይምራል ጌታ

ሳያቅማማ ለአፍታ

ላያስበው መልሶ

እንባን ከዓይን አብሶ

ይቅር ይላል ፈውሶ (፪x)

አላውቀውም ቢል ቢምል ቢክድም

ራሱን ሊያድን ራሱን ቢወድም

መልሶ ሲያዝን ሲፀፀት አየው

የመንግሥቱን ቁልፍ በእጁ አስጨበጠው

ጌታ ይምራል ጌታ ይረሳል

ኃጢአትን ደግሞ መቼ ያስታውሳል

የማረኝ ነኝ የተወልኝ

ላያወሳው ላይደግምብኝ (፪x)

ሲምር ይምራል ጌታ

ሳያቅማማ ለአፍታ

ላያስበው መልሶ

እንባን ከዓይን አብሶ

ይቅር ይላል ፈውሶ (፪x)

ኃጢአት ቢያደርግም ምልስ ልብ ይዟል

የምህረቱን ደጅ ፈጥኖ ያንኳኳል

የተጻፈልን ለትምህርት ነው

ምስክሩ ግን እንደ ልቤ ነው

ጌታ ይምራል ጌታ ይረሳል

ኃጢአትን ደግሞ መቼ ያስታውሳል

የማረኝ ነኝ የተወልኝ

ላያወሳው ላይደግምብኝ (፪x)

ሲምር ይምራል ጌታ

ሳያቅማማ ለአፍታ

ላያስበው መልሶ

እንባን ከዓይን አብሶ

ይቅር ይላል ፈውሶ (፪x)

ድርሻውን ወስዶ ትቶ ቢወጣ

እንዲያው ሲባዝን መቅኖውን አጣ

ባሪያ ልሁን ሲል ዕድል ካገኘሁ

የጠበቀው ግን ልጅነቱ ነው

ጌታ ይምራል ጌታ ይረሳል

ኃጢአትን ደግሞ መቼ ያስታውሳል

የማረኝ ነኝ የተወልኝ

ላያወሳው ላይደግምብኝ (፪x)

ሲምር ይምራል ጌታ

ሳያቅማማ ለአፍታ

ላያስበው መልሶ

እንባን ከዓይን አብሶ

ይቅር ይላል ፈውሶ (፪x)

አዶናይ ሮሆሚን

ራፋዬል ሮሆሚን

መሲያሕ ሮሆሚን

ኤል ሮሆሚን

አዶናይ ሮሆሚን

የሱዋ ሮሆሚን

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ