Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አልቀርም በመና

Alqerem Bemena

2007 · ትራክ 1 · 5:41 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አደባባይ ላይ ሊገለኝ የማለ

ነግቶለት እስኪያየው ልቡ እንደማለለ

ሃማ ተሰቀለ (፪x) [1]

አልቀርም በመና ደጁ ላይ መጥናቴ

እግዜር ለድሆቹ ደራሽ ነው ማለቴ (፪x)

በሀዘን ተመቶ ልቤ እንባ ሲያነባ

ደጁ ላይ ቁጭ ብዬ ስርድ : አየኝና

የእኔ ጌታ ራራልኛ

ጌታዬ ራራልኛ (፪x)

የቀደመ መስሎት ጠላቴ ማልዶ ሲያስር ደባ

አስጨመረልኝ ሞገስ አስደረበልኝ ካባ (፪x)

የረቀቀ መስሎት ጠላቴ ማልዶ ሲያስር ደባ

አስጨመረልኝ ሞገስ አስደረበልኝ ካባ (፪x)

ጌታ ከላይ ቀደመ አዋጅ በአዋጅ ተሻረ ሆ

ለእኔም ፀሐይ ወጣልኝ ነጋ ሌቱ ነጋልኝ (፪x)

አደባባይ ላይ ሊገለኝ የማለ

ነግቶለት እስኪያየው ልቡ እንደማለለ

ሃማ ተሰቀለ (፪x) [1]

አልቀርም በመና ደጁ ላይ መጥናቴ

እግዜር ለደሆቹ ደራሽ ነው ማለቴ (፪x)

በሀዘን ተመቶ ልቤ እንባ ሲያነባ

ደጁ ላይ ቁጭ ብዬ ስርድ አየኝና

የእኔ ጌታ ራራልኛ

ጌታዬ ራራልኛ (፪x)

አምላክ አለኝ የታመኑትን ሜዳ የማይጥል (፪x)

አምላክ አለኝ የለመኑትን ሜዳ የማይጥል (፪x)

አምላክ አለኝ የሚያመልኩትን ሜዳ የማይጥል (፪x)

አምላክ አለኝ የሚወዱትን ሜዳ የማይጥል (፪x)

አምላክ አለኝ የታመኑትን ሜዳ የማይጥል (፪x)

አምላክ አለኝ የለመኑትን ሜዳ የማይጥል (፪x)

አምላክ አለኝ የሚያመልኩትን ሜዳ የማይጥል (፪x)

አምላክ አለኝ የሚወዱትን ሜዳ የማይጥል (፪x)

ሲያልምልኝ ቢያድር ጠላቴ እንዴት ማጥ እንድገባ

አስጨመረልኝ ሞገስ አስደረበልኝ ካባ

አስጨመረልኝ ሞገስ አስደረበልኝ ካባ (፪x)

ጌታ የምስኪን ደራሽ

እንባ ጸሎትን መላሽ ኦ

ሰማ ሰምቶ መጣልኝ

ደርሶ ሳቅ አረገልኝ ሆ (፪x)

ያስጥላል በመላ የእኔ ጌታ አውሬ እንዳይበላ (፪x)

አለው ምህረትህ ለጸኑት ባለመነሳት

አለው ምህረትህ ለጸኑት ባለመነሳት (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ