Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እያባበለኝ

Eyababelegn

2007 · ትራክ 13 · 7:24 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ቀን ጠብቆ ገሸሽ ይልብኝ ይሆን ወይ?

አለልኝ ስል ዓይንሽ/ህ ለአፈር ይለኛል ወይ?

ብዬ እንዳልል እንዳልሰጋበት ዛሬም

አብሮኝ አለ ቤቴ ባይመቸውም

ብዬ እንዳልል እንዳልሰጋበት ዛሬም

አብሮኝ አለ ቤቴ ባይመቸውም (፪x)

እርሱማ እየበደልኩት ቻለኝ

እርሱማ እየራቅኩት ቀረበኝ

እርሱማ ሰለቸኝ ወዲያ አላለኝ (፪x)

ብሸሸው ብርቀው አለቅ ያደረገኝ

ጌታ አይደል ወይ ጌታ አይደለም ዎይ?!

ከ'ነማንነቴ የወደደኝ ጌታ አይደለም ዎይ?! (፪x)

እያባበለኝ (፫x)

ተሸከመኝ (፫x)

በምክሩም ሲያስተምረኝ ደጉን ሲያሰየኝ

እንደ አባት ሲቀጣኝ

ፍቅር ማለት ምን እንደሆነ አወኩኝ

መልሶ ሲያባብለኝ አለው ሲለኝ ሲያበረታታኝ

ፍቅር ማለት ምን እንደሆነ አወ'ኩኝ (፪x)

እያባበለኝ (፫x)

ተሸከመኝ (፫x)

ቀን ጠብቆ ገሸሽ ይልብኝ ይሆን ወይ?

አለልኝ ስል ዓይንሽ/ህ ለአፈር ይለኛል ወይ?

ብዬ እንዳልል እንዳልሰጋበት ዛሬም

አብሮኝ አለ ቤቴ ባይመቸውም (፪x)

እርሱማ እየበደልኩት ቻለኝ

እርሱማ እየራቅኩት ቀረበኝ

እርሱማ ሰለቸኝ ወዲያ አላለኝ (፪x)

ከሞት አፋፍ ነጥቆ ተስፋን የጨመረልኝ

ጌታ አይደል ወይ ጌታ አይደለም ዎይ?!

የተቆረጠውን የቀጠለልኝ ጌታ አይደለም ዎይ?! (፪x)

እያባበለኝ ፣ እያባበለኝ ፣ እያባበለኝ

ተሸከመኝ ፣ ተሸከመኝ ፣ ተሸከመኝ (፫x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ