የዝማሬው ጉልበት
Yezemariew Gulbet
2007 · ትራክ 10 · 4:36 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የዝማሬው ጉልበት ያለው በአፌ ላይ (፪x)
ለአምላኬ የክብሩ ሙዳይ
ለጠላቴ የበረዶ ድንጋይ
ለእግዚአብሔር የክብሩ ሙዳይ
ለጠላቴ የበረዶ ድንጋይ
የዝማሬው ቅባት ያለው በእኔ ላይ (፪x)
ለአምላኬ የክብሩ ሙዳይ
ለጠላቴ የበረዶ ድንጋይ
ቁጥር 1 · Verse 1
ለእግዚአብሔር የክብሩ ሙዳይ
ለጠላቴ የበረዶ ድንጋይ
ሰልፉን አይቼ ልቤ ሲርድ
በእጃቸው ገባሁ ዛሬ ሳልወድ
ብዬ አምላኬን ምነው ስል
ትዕዛዝ አወጣ እንዲህ ሲል፦
ማለዳ ቆሜ ተራራ ላይ
ክብሬን ዘምሪ ክብር እንድታዪ
እኔም ሰምቼው ስዘምር
ሰደደባቸው ድብቅ ጦር
ማልጄ ሆ ብዬ እነሳለሁ ከበሮዬን አነሳለሁ
ለአምላኬ ስዘምርለት ይርዳል የጠላቴ ጉልበት
ማልጄ ሆ ብዬ እነሳለሁ በገናዬን አነሳለሁ
ለአምላኬ ስዘምርለት ይፈታ የጠላቴ ጉልበት
አዝማች · Chorus
የዝማሬው ጉልበት ያለው በአፌ ላይ (፪x)
ለአምላኬ የክብሩ ሙዳይ
ለጠላቴ የበረዶ ድንጋይ
ለእግዚአብሔር የክብሩ ሙዳይ
ለጠላቴ የበረዶ ድንጋይ
የዝማሬው ቅባት ያለው በእኔ ላይ (፪x)
ለአምላኬ የክብሩ ሙዳይ
ለጠላቴ የበረዶ ድንጋይ
ቁጥር 2 · Verse 2
ለእግዚአብሔር የክብሩ ሙዳይ
ለጠላቴ የበረዶ ድንጋይ
ወደ ጓዳዬ እንደለመድኩት
ለአምላክ ስዘምር እንዳደግኩት
ዛሬ አደባባይ ወጣሁና
ሥሙን ጠራሁት እንደገና
ብላቴኖችን የሚወደው
እግዚአብሔር ቀባኝ አትበሉ እንዴት ነው
ክፉ መንፈስ አይቶኝ ሲሸሽ
ጌታ ይከብራል ነግቶ እስኪመሽ
ማልጄ ሆ ብዬ እንነሳለሁ ከበሮዬን አነሳለሁ
ለአምላኬ ስዘምርለት ይርዳል የጠላቴ ጉልበት
ማልጄ ሆ ብዬ እንነሳለሁ በገናዬን አነሳለሁ
ለአምላኬ ስዘምርለት ይፈታ የጠላቴ ጉልበት
አዝማች · Chorus
የዝማሬው ጉልበት ያለው በአፌ ላይ (፪x)
ለአምላኬ የክብሩ ሙዳይ
ለጠላቴ የበረዶ ድንጋይ
ለእግዚአብሔር የክብሩ ሙዳይ
ለጠላቴ የበረዶ ድንጋይ
የዝማሬው ቅባት ያለው በእኔ ላይ (፪x)
ለአምላኬ የክብሩ ሙዳይ
ለጠላቴ የበረዶ ድንጋይ
ቁጥር 3 · Verse 3
ለእግዚአብሔር የክብሩ ሞዳይ
ለጠላቴ የበረዶ ድንጋይ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ