Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የእግዚአብሔር እጅ

YeEgziabhier Ej

2007 · ትራክ 9 · 5:35 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የእግዚአብሔር እጅ የያዘው ነገር

እንዳይወድቅ አይፈራ እንዳይጠፋ አይፈራ

ከጥላው ሥር ያረፈው ሰው

ዘላለሙ አያሰጋው (፪x)

አባትዬ የእኔ ወዳጅ (፪x)

ኑሮዬ በአንተ እጅ (፪x)

አባትዬ የእኔ ከለላ ከለላዬ

በጥላህ ሥር ነው ማደሪያዬ (፪x)

በእናቴ ማህፀን ደም ሳለሁኝ አጥንቶቼም ሳይዋደዱ

አንተው ታውቀው ነበር እንዲህ እንዲሆን የሕይወቴ አካሄዱ

ደግሞስ ካሳለፍከኝ በቸርነትህ የትላንቱን ጨለማ

ለነገውስ ቢሆን ለምን አላምንም ሕይወቴ በእጅህ ነውና

ተውኩት ሁሉንም ለአንተ ተውኩት

ተይ ነፍሴ እኔ አላውቅም ብዬ እንዳልኩት

ይሁን ያልከው የፀና ለመሆኑ

ምስክር ነው ሰማይ ያለ ማገር መቆሙ

የእግዚአብሔር እጅ የያዘው ነገር

እንዳይወድቅ አይፈራ እንዳይጠፋ አይፈራ

ከጥላው ሥር ያረፈው ሰው

ዘላለሙ አያሰጋው (፪x)

አባትዬ የእኔ ወዳጅ (፪x)

ኑሮዬ በአንተ እጅ (፪x)

አባትዬ የእኔ ከለላ ከለላዬ

በጥላህ ሥር ነው ማደሪያዬ (፪x)

ክብርን የምትገልፅበት ደካማ ሰው ስትፈልግ አገኘኸኝ

እንጂማ በእራሴ እንኳን በአንተ በሰውም ዓይን የማልሞላ ነኝ

ግና ከወደድከኝ በዓይነህ ከታየሁ እኔስ ምን እልሃለሁ

አንተ ነህ ደጀኔ ተባረክልኝ ከትከሻህ የሚያወርደኝ ማነው

አልጥልሽ አልተውሽ እያልክ

ልቤን ስትደግፈኝ እንደዋልክ

አይቼህ መንፈሴ ረካ

አትተወኝም አትረሳኝም ለካ

አዬ አትረሳኝም ለካ

አትተወኝም በቃ አትረሳኝም በቃ

አሄ አትረሳኝም በቃ

አትተወኝም በቃ አትለቀኝም በቃ

አሄ አትለቀኝም በቃ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ