ብዛልኝ
Bizalign
2024 · ትራክ 8 · 5:50 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አንተ የሌለህበት ቦታ ለምኔ
ሃገር ለምኔ ከፍታ ለምኔ
አንተ የሌለህበት ህብረት ለምኔ
መዝሙር ለምኔ ወሬ ለምኔ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
አስጠጋኝ ወደ እቅድህ
ወዳየህልኝ ወደ ሃሳብህ (፪x)
የእግሮቼን ጉዞ መትርልኝ
የአንደበቴን ቃል ስፈርልኝ
ለፈቃዴ ገደብን አብጅለት
ሞገደኛው ልቤ ይወቅ ለከት
አስተምረኝ ምን ትላለህ ማለት (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አይኖቼ እያዩ ቅጥቅጧን ሸንበቆ ደግፈህ ስታቆመኝ
እያወቀ ልቤ የምጤሰውን ጧፍ ቀርበህ ስታበራኝ
ጆሮዬ እየሰማ ለራስ ማልበቃውን ስታተርፈኝ ለሃገር
በቀረልኝ እድሜ ከአንተ ሌላ ውጪ አፌ ምን የናገር
አሁንም ብዛልኝ እንዲረዝም እድሜዬ
አብልጬ ልጠጋህ እንዲደምቅ ማታዬ
ሁነኝ መዋያዬ በቀረልኝ ዘመን
መንገዴ እየነጋ እስኪሆን ሙሉ ቀን (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ዉሎ ካንተ ጋር አድሮና ሰንብቶ
ማን በትናንት ቀረ ከአንተ ብዙ ቀድቶ
የለውጥ ጅማሬ ነህ የሕይወት ማጣፈጫ
የተጠጉህ ሁሉ ወጥተዋል በብልጫ (፪x)
ሰሞነኛ እንዳልሆን አድሮ እንዳልሰለች
ጉልበቴን ላስጠጋ ወደ ቃሎችህ ደጅ
ዘመንን ዘላቂ እንዲሆን ነገሬ
ዙረቴን አቁሜ ልፈልግህ ዛሬ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ