Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ጉዳዬ

Gudaye

2024 · ትራክ 2 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ለሚያወራህ ውበት ለሚለብስህ ጌጥ

ሮጦ ለተጠጋህ የማምለጫ አለት

ህይወት ከሞት ወዲያ እርስቱ ላረገህ

ለአፍታ እንኩዋን የማትጎድል ለሰው ሙላቱ ነህ

አንተን ነው እንጂ

ጥብቅ አድርጎ መያዝ ያዘኝ እያሉ

ማልዶ በጠዋት

በአንተው እጅ ነቅቶ መዋል ደጅ እየጠኑ (፪x)

ዓይኔን ጉዳዬ ላይ ማድረግ

ፍለጋዬን እድሜ ልክ መፈለግ

ናፍቆቴን ሳላርፍ መናፈቅ

ጉጉቴን ሳልደክም መፈለግ

እንዲሆንልኝ ይብዛልኝ ጸጋህ

ጊዜው ደርሶ እስክደርስ አንተ ጋር

ገባ ወጣ እግሬ ሳይልብኝ

ፍለጋዬ ሳትጎድል ብዛልኝ

በድነቴ ጠዋት በገባኸኝ ማግስት

ጨዋታ ወሬዬ መወደዴን ማድነቅ

ዘምሬህ አልጠግብ አውርቼህ አልረካ

ይህቺ ትንሽ ልቤ ለፍቅርህ ሸፍታ

አልደግ አንተ ላይ እራሴን አልቻል

አጓጉል ነው ሁሉም ያላንተ መች ያምራል

መጠበቂያ አጥሬ መሰንበቻዬ ነህ

ልኑር እንደፈዘዝሁ ዓይኔ አንተን እያለ

ጉዳዬ አንተው መናፈቄ መምጣትህ

ጉጉቴ ዓይኔ እስከሚያይህ

ሁሌ ሁሌ ሁሌ ሁሌ አንተን ብቻ

እስከ እድሜዬ መቋጫ (፬x)

ዓይኔን ጉዳዬ ላይ ማድረግ

ፍለጋዬን እድሜ ልክ መፈለግ

ናፍቆቴን ሳላርፍ መናፈቅ

ጉጉቴን ሳልደክም መፈለግ

እንዲሆንልኝ ይብዛልኝ ጸጋህ

ጊዜው ደርሶ እስክደርስ አንተ ጋ

ገባ ወጣ እግሬ ሳይልብኝ

ፍለጋዬ ሳትጎድል ብዛልኝ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ