Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ወደ ተራራው ጫፍ

Wede Teraraw Chaf

2024 · ትራክ 9 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ከህልውናህ ሰፈር ከምትገኝበት

ንግግር ፀሎቴ አንተው ከሆንክበት

ጠንቀቅ ካላልኩኝ ካልጠበቅሁ እግሮቼን

እልፍ የሚለይ ጉዳይ ከቦኛል ዙሪያዬን

በገለባ ናፍቆት በጠፊ ፍለጋ

አይለፍብኝ ቀኔ አርቆኝ ካንተ ጋር

ወደተራራው ጫፍ ሳበኝ ወደራስህ

ነፍሴም ድና እንድትቀር አቅልጣት በክብርህ (፪x)

መባዘን አይደለም መዋል ካንተ ጋራ

ስለ ላዩ ምክርህ ነፍሴን ስታዋራ

ሰብሰብ ብሏል ቀኔ አልተዝረከረከም

የማይወሰድ እድል ከዚህ በላይ የለም

አንተን ብቻ ይሁን የማይበት ዓይኔ

ልቤም ሄዶ ይቅር ከላዩ ሰፈሬ

ጆሮዬም ይቀስር ከላይኛው ሃገር

አጥፋኝ ከምድሩ ፍለጋዬ ይሰወር

አንገቴን አስግጌ በመናፈቅ ህይወት

ለአፍታ ጎንበስ ሳልል አንዳች ከሌለበት

እጅ ሰጥቶ ላንተ ውስጥና ውጪዬ

ስንቄ ሆኖ ፍቅርህ ይጠቅለል እድሜዬ (፪x)

ጥሜ ረሃቤ ናፍቆቴ መሻቴ

ጉጉቴ ፍላጎቴ ሩጫዬ መገስገሴ

አንተን ለማግኘት ነው (፪x)

በቃ ፈልግሃለሁ በቃ ተርቤሃለሁ

በቃ በጣም ጠምተኸኛል በቃ አይኖቼ ናፍቀውሃል

በቃ ናፍቄሃለሁ በቃ ደጅ ደጅ አያለሁ

በቃ የውስጤ ጥም ነህ

በምንም የማልለውጥህ

አንተን የተራበ ሚጠግበው አንተን ነው

አንተን የተጠማ ሚረካው አንተን ነው

ፊትህን የፈለገ ሲያገኝህ ያርፋል

ፈልጎ ክብርህን መቼ በጅህ ይረካል

አይደለሁም ሰነፍ ተመከርኩ በቃልህ

የውስጤን እረሃብ አይደፍነውም የእጅህ

ነፍሴን የምታረካ ሙላት ነህ የልቤ

የኑሮዬ ፍሰሃ የዕድሜ ልክ ሃሳቤ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ