አመልክሃለው
Amelkihalehu
2024 · ትራክ 6 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እረሳሁት ጥያቄዬን
የከበበኝን በዙሪያዬ
ስቀርብ ፊትህ ለማመስገን
ቀሎ ታየኝ ሁሉም ነገር (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሳላመልክህ ጊዜው አይለፍ
የሚገባህን ምስጋና ሳላቀርብ
ሞልቶ ላይሞላ የምድሩ ነገር
ካልክልኝ አልጎድልም ለጭንቅ ውሎ ማደር
ርቋል ከኔ ሰፈር (፪x)
አዝማች · Chorus
አመልክሃለው (፫x) በማደሪያዎችህ መካከል ቆሜ
አመልክሃለው (፫x) በማደሪያዎችህ መካከል ቆሜ
ለተራራው ቁመት እያልኩኝ ትልቅ ነህ
ለሸለቆው ጥልቀት እያልኩኝ ሙላት ነህ
ለሞገዱ ብርታት እያልኩኝ ሰላም ነህ
ለጨለማው ርዝመት እያልኩኝ ብርሃን ነህ
አመልክሃለው (፫x) በማደሪያዎችህ መካከል ቆሜ
ቁጥር 3 · Verse 3
ብዙ ጊዜ ታገልኩ ከቃላቶች ጋራ
ስላንተ ማንነት በዝርዝር ላወራ
አንሰው ተገኙብኝ ያለኝ ሁሉ አላረካኝ
እንደገባኝ መጠን እንኳን ልገልጽህ አቃተኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
ማንም እንደሚልህ አይደለህም
ከመታወቅ ታልፋለህ
እግዚአብሔር ትልቅ ነህ (፪x)
ትልቅ ነህ (፪x) እግዚአብሔር ትልቅ ነህ (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ካነበብኩት አይደል ከሰው የሰማሁት
ዛሬ በዚህ ሰዓት ፊትህ ያመጣሁት
ከነፍሴ ምስጋና ከውስጠቷ የሆነ
አፌን ሞልቶ የሚፈስ አዲስ ቅኔ አለ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ያላነሰ ያላጠረ
ከላይ ከላይ ያልሆነ
ለእኔ ፍቅር ለኢየሱሴ
አለኝ ምስጋና ከነፍሴ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ