Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ሃሌሉያ

Hallelujah

2024 · ትራክ 3 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በሰላሙ ብዛት ቀለለ ችግሩ

አደገ ቁመቴ እያለ ነገሩ

ቀረ መዋከቤ በጠራኸኝ ሳርፍ

ተምራልኝ ነፍሴ አንተ ላይ ማራገፍ

ድምጿ ተቀየረ ተለወጠ ቃ

እዬዬን በእሰየው የአንተ በመሆኗ

እህህን በእልልታ ለምኑን በአሜን

ለለወጥከው እየሱስ እንካ ዘላለሜን

እዬዬን በእሰየው የአንተ በመሆኗ

እህህን በእልልታ ለምኑን በአሜን

ለቀየርከው እየሱስ እንካ ዘላለሜን

ተባረክ እልሃለሁኝ (፰x)

ተንበርክኬ አሸነፍኩኝ

እጅ ሰጥቼ ድል ነሳሁኝ

በጩኸቴ መዳን ሆነ

አበሳዬ ተከደነ

ተከትዬህ ከፊት ቀደምኩ

ያንተን ብዬ ከምን ጎደልኩ

ስፈልግህ ጸኑ እግሮቼ ሃይሌ ሆነኸኝ ተሟጋቼ

በመጨነቅ ስርአትህን

በመማጸን መጓደድን

በር በመዝጋት ክፉን ማምለጥ

እርዳኝ ብዬ ሁሉን መብለጥ

ከአንተ ሰምቶ የውስጥ ውበት

አቤት ብዬህ አለኝ ማለት

ከአንተ ዘግኖ ሞልቶ ማደር

ሆኖልኛል ስምህ ይክበር

ስኬቴ በአንተ መታመኔ

ከፍታዬ እግርህ ስር መሆኔ

ውበቴ አንተን መጠጋቴ

ድምቀቴ ምህረትህ ነው ለኔ

ስኬቴ በአንተ መታመኔ

ከፍታዬ እግርህ ስር መሆኔ

ውበቴ አንተን መጠጋቴ

ድምቀቴ ምህረትህ ነው ለኔ

አሃ ሃሌሉያ/4 እላለሁ ሃሌሉያ

በማለዳ ሃሌሉያ በቀትር ሃሌሉያ

በምሽት ሃሌሉያ በሌሊት ሃሌሉያ

ሁሉ እንዳለ ሆኖ ሃሌሉያ

ሳይቀየር ሃሌሉያ

እላለሁ ሃሌሉያ

አሃ ሃ ሃ ሃሌሉያ (፪x)

ኦሆ ኦሆ ኦሆ ሃሌሉያ

አሃ ሃ ሃ ሃሌሉያ (፫x)

ኦሆ ኦሆ ኦሆ ሃሌሉያ

አሃ ሃ ሃ ሃሌሉያ

ኦሆ ኦሆ ኦሆ ሃሌሉያ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ