ፍለጋው አደረገኝ
Filegaw Aderegegn
2024 · ትራክ 5 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እንደገናን ባያውቅ ዳግም ዕድል ባይሰጥ
ማን ይችል ነበረ የጌታን ደጅ ሊረግጥ
እየተደገፈ በማይሰፈር ፀጋው
እንደኔ የቆመ ስንቱን ቤት ይቁጠረው
ቁጥር 2 · Verse 2
ስንቱን ቤት ይቁጠረው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ደጋግሞ የተፈተነ እምነቴ
እንዳይንኮታኮት አልቆለት እንዳይወድቅ
እንደስንዴ ሊያበጥረኝ የወጣውን ፈታኝ
በ ‘አይቻልም’ ሲሰድ
የአንደበቴን ሳይሆን ያወቀ የልቤን
እንደተመኘሁት ልሆን ያለመቻሌን
እስኪቆሙ እግሮቼ በብዙ አገዘኝ
ሃይልን እስክቀበል አይዞሽ በርቺ እያለኝ
ያለቀልኝ መስሎት ለሳቀብኝ ጠላቱ
ቁጥር 4 · Verse 4
ማልዶ ማለደልኝ ጉልበቴን አጸናት (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ክህደት መሃላዬን አላውቀውም ማለቴን
ዶሮ ሶስቴ እስኪጮህ አልፎ መጨመሬን
ከትንሳኤው ማግስት ብርቱዎች እያሉ
ከሰነፎች ተርታ እንደኔ ያልዋሉ
ፍልጋው አረገኝ መጣ ወዳለሁበት
ሊቀጥለኝ ዳግም ከተቆረጥኩበት
ቁጥር 6 · Verse 6
ፍለጋው አደረገኝ መጣ ወዳለሁበት (፬x)
ቁጥር 7 · Verse 7
በማይጠቅሙት መጠቀም ልማዱ ለሆነው
በማለዳ ምስጋናዬ ይኸው
በማይጠቅሙት መጠቀም ልማዱ ለሆነው
ለተቤዠኝ ምስጋናዬ ይኸው
በማይጠቅሙት መጠቀም ልማዱ ለሆነው
ሳላቋርጥ ምስጋናዬ ይኸው
አዝማች · Chorus
በትንሽ አዕምሮዬ ስላሰብኩት ነገር
ብዕሬን ይዣለው ቃላትን ቀምሬ በዜማ ልናገር
አልችልም ልደብቅ የውስጥ ደስታዬን
እሱ በኔ ሆኖ ነውሬን አስወግዶ ከሰው መቆጠሬን
ዝም ይባላል እንዴ ደግሞስ ያስችላል ወይ
አትረፍርፎ አድርጎልኝ ረድኤቱን ከላይ
የቃላትን ድንበር ጥሶ ያለፈ መውደድ
አንድ ልጁን ሰጥቶ የራሱ የሚያደርግ
ቁጥር 8 · Verse 8
አጽናንቶኛል ባድማ ህይወቴን በመልካምነቱ ሞልቶ
አስደሰተኝ በረሃ ህይወቴን እንደ ኤደን አድርጎ
ተድላ አደለኝ የደስታ የቅኔ ድምጽ ወጣ ከቤቴ
መራቄ ቀርቶ ቀርቤአለሁ አብ ሆኖኝ አባቴ (፪x)
አዝማች · Chorus
በትንሽ አዕምሮዬ ስላሰብኩት ነገር
ብዕሬን ይዣለው ቃላትን ቀምሬ በዜማ ልናገር
አልችልም ልደብቅ የውስጥ ደስታዬን
እሱ በኔ ሆኖ ነውሬን አስወግዶ ከሰው መቆጠሬን
ዝም ይባላል እንዴ ደግሞስ ያስችላል ወይ
አትረፍርፎ አድርጎልኝ ረድኤቱን ከላይ
የቃላትን ድንበር ጥሶ ያለፈ መውደድ
አንድ ልጁን ሰጥቶ የራሱ የሚያደርግ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ