እዩልኝ
Eyulign
2024 · ትራክ 11 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እዩልኝ
ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ /3
ላውራው ልዘምረው
ልናገር ልተርከው
ልጥራው ልደጋግመው
ልመርኮዝ ልደገፈው
ስሙ ከፊደል ያለፈ ነው
ስሙ ከአንድ ቃል ያለፈ ነው
ስሙ ከስሞች ያለፈ ነው
ስሙ ከምለው ያለፈ ነው
ስምህን ስጠራው ጥሜ ይረካልኛል
ስምህን ስጠራው ከረሃቤ እጠግባለሁኝ/፪
ቁጥር 2 · Verse 2
ለዚህ ነው ሲነጋም ኢየሱስ የምለው
ለዚህ ነው በቀትር ኢየሱስ የምለው
ለዚህ ነው ሲመሽም ኢየሱስ የምለው
ለዚህ ነው በሌሊት ኢየሱስ የምለው
ቁጥር 3 · Verse 3
በምን አጎደልከኝ መች ጠናሁ የሰው ደጅ
ከጫፍ ጫፍ ሙላት የምትደላ የምትመች
ሰው እንኳን የሚያልፈውን ይኼ አለኝ ይላል
አንድ ሁለት ሶስት ብሎ ያስቆጥራል
የማታልቅ የማታልፍ የማትደክም ትምክህቴ
የማልቀይርህ መዝሙር እስካለሁ በህይወቴ
ለልጅ ልጅ ትምህርት ርስትም ያለኸኝ
ለሚያዩኝ ሁሉ እዩልኝ የሚያስብለኝ
አዝማች · Chorus
እዩልኝ እዩልኝ ደግነቱን እዩልኝ
እዩልኝ እዩልኝ ምህረቱን እዩልኝ
ቁጥር 4 · Verse 4
እዩልኝ እዩልኝ ደግነቱን እዩልኝ
እዩልኝ እዩልኝ ምህረቱን እዩልኝ
ቁጥር 5 · Verse 5
ከማይደረስበት ከቅድስናው ጥግ በሞቱ አድርሶኝ
ጸድቀሻል አለኝ እዩልኝ
ካለሁበት ሸለቆ ህያው ቃሉን ልኮ ዳግም ሰው አርጎኝ
አንቺ ብርቱ አለኝ እዩልኝ
አዝማች · Chorus
እዩልኝ እዩልኝ ደግነቱን እዩልኝ
እዩልኝ እዩልኝ ምህረቱን እዩልኝ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ