እግዚአብሔር እንደ ጨካኝ
Egziabhier Ende Chekagn
ትራክ 4 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እልፍ እያለ የሚሄድ የኋላውን ጥሎ
የጌታውን ፍለጋ ዱካውን ተከትሎ
አስቀድሞ ይወጣል ልቡን እያስደፈረ
አስተውሎ ያደርጋል ዘመን እየመረመረ (፪x)
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር እንደ ጨካኝ እንደ ኃያል
በጠላቶቼ ላይ ወረደ እያንዳንዱን ሊበቀል (፪x)
ጠጠር ይዞ የማይፈራ አሃሃ
የጠላቶቹ ዛቻና ፉከራ እህህ (፪x)
ከአምላኩ የተማረው የሰማ ነው ያሸነፈው (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ህዝቡን ያሸበረው እስኪ የቱ ነው ብሎ
ከሰልፉ መሃል ይወጣል በአምላኩ ተማምሎ
ዋነኛውን ሳይጥለው እርሱ አያፈገፍግም
ጭፍራውን ሳይበትነው ደግሞ አይመለስም (፪x)
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር እንደ ጨካኝ እንደ ኃያል
በጠላቶቼ ላይ ወረደ እያንዳንዱን ሊበቀል (፪x)
ጠጠር ይዞ የማይፈራ አሃሃ
የጠላቶቹ ዛቻና ፉከራ እህህ (፪x)
ከአምላኩ የተማረው የሰማ ነው ያሸነፈው (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ይሄስ የማነው ጀግና የማነው እርሱ
ይሄስ የማነው ጐበዝ የማነው እርሱ (፪x)
አሳየው እንጂ ቆርጠህ እራሱን
አሳየው እንጂ ቆርጠህ አንገቱን (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ