Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ያመንኩትን አውቃለሁ

Yamenkuten Awqalehu

ትራክ 9 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ያመንኩትን አውቃለሁ የተረዳሁትን

አንዱም አይጣል ከእርሱ የሰማሁት

በእጄ እንዳለ እንደጨበትኩት

ያህል ነው የምቆጥረው እንደያዝኩት (፪x)

አምላኬ አምላኬ እርሱ ይታመናል

ከተናገረው የቱንስ አስቀርቷል

አምላኬ አምላኬ እጅግ ይታመናል

ካለበት ቀን እልት መቼ ፈቀቅ ብሏል (፪x)

እለት እለት እርሱን ሳወጣና ሳወርደዉ

ቃሉን በአፌ አኑሬ እርሱን ብቻ ሳመላልሰዉ

ጥቅልሉን ስፈታ ውሉን ይዤ ስተረትረዉ

በዓይን ያልታየው ይገለጣል ጆሮ ያልሰማው (፪x)

ቃል ከአፉ ሲወጣ አልጠራጠረዉም

በልቤ አኑሬ እምጠባበቀዉም

ፈጽሞ አይሆንልኝ ችላ ችላ ማለት

እይዘለለ ውስጤ መች ይሰጠኝ እረፍት (፪x)

አምላኬ አምላኬ እርሱ ይታመናል

ከተናገረው የቱንስ አስቀርቷል

አምላኬ አምላኬ እጅግ ይታመናል

ካለበት ቀን እልት መቼ ፈቀቅ ብሏል (፪x)

ጌታዬ ብዬ አመልክሃለሁ

ወዳጄ ብዬ አመልክሃለሁ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ