Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ቀናቶቼ በከንቱ

Qenatochie Bekentu

ትራክ 6 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ቀናቶቼ በከንቱ ዓመታቶቼ በችኮላ

እንዲሁ እንዳያልፉ ከዚህ በኋላ

ዘመኔን በሙሉ በፊቴ ያለውን

ያለ ፍሬ እንዳልሆን አስታጥቀኝ ኃይልን

ነፍሴ በኃይል በኃይል በኃይል እርግጥ ይሂ (፪x)

ወደላይ ወደላይ ወደላይ ውጪ (፪x)

ነፍሴ በኃይል በኃይል በኃይል እርግጥ ይሂ

እልፍ እልፍ እልፍ አያልኩኝ

የኋላዬን ወደኋላ እየተውኩኝ

የተያዝኩበትን ለመያዝ ፈጥናለሁ

ያለዋላ ማየት ሌላ ምን እሻለሁ

ነፍሴ በኃይል በኃይል በኃይል እርግጥ ይሂ (፪x)

ወደላይ ወደላይ ወደላይ ውጪ (፪x)

ነፍሴ በኃይል በኃይል በኃይል እርግጥ ይሂ

ስለእኔ የሚያስበው ዘውትር መልካም ነው

በጅምር የማይቀር ፍጻሜ ያለው

የሚዳሰስ የሚጨበጥ አያለሁ ከዚህ የሚበልጥ (፪x)

(የሚጠነቀቅልኝ)

የሚዳሰስ የሚጨበጥ አያለሁ ከዚህ የሚበልጥ (፪x)

ላልመለስበት እኔን ያስመለጠ

ብርሃኑን ልኮ ከእጆቼ ያስጣለ

እንደ ዓይኑ ብሌን የሚጠነቀቅልኝ

የታቹን አስጥሎ የላዩን አስያዘ

ነፍሴ በኃይል በኃይል በኃይል እርግጥ ይሂ (፪x)

ወደላይ ወደላይ ወደላይ ውጪ (፪x)

ነፍሴ በኃይል በኃይል በኃይል እርግጥ ይሂ

የሚዳሰስ የሚጨበጥ አያለሁ ከዚህ የሚበልጥ (፪x)

(የሚጠነቀቅልኝ)

የሚዳሰስ የሚጨበጥ አያለሁ ከዚህ የሚበልጥ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ