መተማመኛዬ
Metemamegnayie
ትራክ 1 · አማርኛ
መተማመኛዬ የተማመንኩበት
አያሳፍረኝ የተደገፍኩት
በፍፁም አልሰጋ ግራም አይገባኝ
ሊያደርግ ያለውን ከእኔ አይሰውረኝ (፪x)
የእኔ ጌታ የታመነዉ
ቃሉን በሥራ የገለጠዉ
የእኔ ኢየሱስ የታመነዉ
በስጦታው አይጸጽተዉ (፪x)
ታማኝነቱ አጥብቆ ያዘኝ
መቼም ከእጆቹ እኔን ላይለቀኝ
በእኔ መጨከን አይሆንለት
ምህረቱ ብዙ የእሱስ አያልቅም
ልበለው እንጂ ተባረክ (፫x)
አትለወጥም ተባረክ (፫x)
አንተ ታማኝ ነህ ተባረክ (፫x)
ተባረክ ጌታ ተባረክ
ተባረክ ሁሌ/ዘለዓለም ተባረክ (፪x)
በጌታ ተማምኖ ከመንገድ የቀረ
ማን አንገቱን የደፋ ማን ያቀረቀረ
አታፍሪም እንዳለ መቼ ያሳፍራል
ከመቅደሱ ሆኖ ድሉን ያፈጥነዋል (፪x)
የእኔ ጌታ የታመነዉ
ቃሉን በሥራ የገለጠዉ
የእኔ ኢየሱስ የታመነዉ
በስጦታው አይጸጽተዉ (፪x)
ታማኝነቱ አጥብቆ ያዘኝ
መቼም ከእጆቹ እኔን ላይለቀኝ
በእኔ መጨከን አይሆንለት
ምህረቱ ብዙ የእሱስ አያልቅም
ልበለው እንጂ ተባረክ (፫x)
አትለወጥም ተባረክ (፫x)
አንተ ታማኝ ነህ ተባረክ (፫x)
ተባረክ ጌታ ተባረክ
ተባረክ ሁሌ/ዘለዓለም ተባረክ (፭x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ