አመሰግናለሁ
Amesegenalehu
ትራክ 2 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሁልጊዜ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ
ዘወትር እርሱን ብቻ እባርካለሁ
መሸ ብዬ አልልም እስኪነጋም አልጠብቅም
ሌቱም እያቅላላ ቀን እንዲሆን አውቃለሁ
ደጋግሜ ሳመሰግን ሥሙን እየጠራሁ
አዝማች · Chorus
ጌታ ነው አሃሃ አምላክ ነው ኦሆሆ
ሁሌ ሲሰራ አሃሃ ትክክል ነው ኦሆሆ
አደራረጉ አሃሃ ልዩ ነው ኦሆሆ
ተዓምራቱ ኦሆሆ ብዙ ነው
ቁጥር 2 · Verse 2
እስኪ ላመስግነው ቃላቴ ይሰማ
ልቤ ከአንደበቴ ጋር እየተስማማ
ሌላ ሌላው ይቅር ስለእርሱ ልናገር
እጆቼም ይነሱ ስለሥሙ ክብር
አዝማች · Chorus
ይኼ ጌታ የሁሉ ጌታ ነው አኸኸ (፫x)
የበላይ የበላይ ሁሌም የበላይ ነው አኸኸ (፫x)
ይኼ ጌታ የሁሉ ጌታ ነው አኸኸ (፫x)
የበላይ የበላይ ሁሌም የበላይ ነው አኸኸ (፫x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ታላልቁ ሥራው ድንቅ ተዓምራቱ
ትኩር ብዬ ሳየው የእርሱ በጐነቱ
አላስቀምጥ አለኝ እየቀሰቀሰኝ
አመሰግነዋለሁ ተራው ስለደረሰኝ
አዝማች · Chorus
ይኼ ጌታ የሁሉ ጌታ ነው አኸኸ (፫x)
የበላይ የበላይ ሁሌም የበላይ ነው አኸኸ (፫x)
ይኼ ጌታ የሁሉ ጌታ ነው አኸኸ (፫x)
የበላይ የበላይ ሁሌም የበላይ ነው አኸኸ (፫x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ሁልጊዜ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ
ዘወትር እርሱን ብቻ እባርካለሁ
መሸ ብዬ አልልም እስኪነጋም አልጠብቅም
ሌቱም እያቅላላ ቀን እንዲሆን አውቃለሁ
ደጋግሜ ሳመሰግን ሥሙን እየጠራሁ
አዝማች · Chorus
ይኼ ጌታ የሁሉ ጌታ ነው አኸኸ (፫x)
የበላይ የበላይ ሁሌም የበላይ ነው አኸኸ (፫x)
ይኼ ጌታ የሁሉ ጌታ ነው አኸኸ (፫x)
የበላይ የበላይ ሁሌም የበላይ ነው አኸኸ (፫x)
ጌታ ነው አሃሃ አምላክ ነው ኦሆሆ
ሁሌ ሲሰራ አሃሃ ትክክል ነው ኦሆሆ
አደራረጉ አሃሃ ልዩ ነው ኦሆሆ
ተዓምራቱ ኦሆሆ ብዙ ነው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ