የቃልኪዳን አምላክ
Yeqalkidan Amlak
ትራክ 3 · አማርኛ
እኔ የማመልከው (፫x)
በመጥራቱ እና በሥጦታው ሁሉ የማይጸጸተው
የቃልኪዳን አምላክ ነው (፫x)
እኔ የማመልከው (፫x)
በመጥራቱ እና በሥጦታው ሁሉ የማይጸጸተው
የቃልኪዳን አምላክ ነው (፭x)
ቃሉን ልኮ መች ይቀራል
እንዳለዉ ከተፍ ይላል
አይመጣ አርፍዶ
ያውቅበታል መድረስ ማልዶ
አመልከዋለሁ (፬x)
ዕድሜ ልኬን ሙሉ ቀኑ እስኪሆን ሙሉ
ዕድሜ ልኬን ሙሉ ቀኑ እስኪሆን ሙሉ (፪x)
አመልከዋለሁ
ማነው እንደ ጌታ ማነዉ ማነዉ
በቀኑ የሚደርስ ማነዉ ማነዉ
እኔስ አላየሁም ማነዉ ማነዉ
እኔስ አላገኘሁም አላየሁም (፬x)
እኔስ አላገኘሁም
ጆሮው ሰምቶ ዝም አይልም
እንዳላየ ሆኖ አያልፍም
ትንሽ ትልቅ ብሎ አይልም
ቃሉን ሊያደርገው ሲቸኩል
አመልከዋለሁ (፬x)
ዕድሜ ልኬን ሙሉ ቀኑ እስኪሆን ሙሉ
ዕድሜ ልኬን ሙሉ ቀኑ እስኪሆን ሙሉ (፪x)
አመልከዋለሁ
ማነው እንደ ጌታ ማነዉ ማነዉ
በቀኑ የሚደርስ ማነዉ ማነዉ
እኔስ አላየሁም ማነዉ ማነዉ
እኔስ አላገኘሁም አላየሁም (፬x)
እኔስ አላገኘሁም
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ