ዛሬም ጉልበታም ነኝ
Zariem Gulbetam Negn
ትራክ 10 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ዛሬም ጉልበታም ነኝ እንደ ትላንቱ
ጉልበቴ አልደከመም አድርጐኝ ብርቱ
መች ይሆንልኛል እኔስ ሳልይዘው
ያንን ተራራዉ
መች ይሆንልኛል እኔስ ሳልይዘው
ያንን ኮረብታዉ
ዛሬም ጉልበታም ነኝ እንደ ትላንቱ
ዛሬም ጉልበታም ነኝ እኔ አልደከምኩ
ምን ቁመቱ ቢረዝም ምን በፊቴ ቢገዝፍ
ምን ቁመቱ ቢረዝም ምን በፊቴ ቢገዝፍ
እኔን በፍፁም አያስፈራራኝ
አዝማች · Chorus
ከእኔ ጋር ያለው ነው አስተማማኝ (፪x)
አሃ አሃ እኔስ አልፈራ
አሃ አሃ አልደነግጥ (፪x)
እርሱ እየሄደ ከእኔ ፊት ፊት
እርሱ እየመራ ከእኔ ፊት ፊት
እርሱ እየወጣ ከእኔ ፊት ፊት
እየቀደመ ከእኔ ፊት ፊት
እኔስ አልፈራ አልደነትጥ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ዛሬም ጉልበታም ነኝ እንደ ትላንቱ
ጉልበቴ አልደከመም አድርጐኝ ብርቱ
መች ይሆንልኛል እኔስ ሳልይዘው
ያንን ተራራዉ
መች ይሆንልኛል እኔስ ሳልይዘው
ያንን ኮረብታዉ
ዛሬም ጉልበታም ነኝ እንደ ትላንቱ
ዛሬም ጉልበታም ነኝ እኔ አልደከምኩ
ጥላቸው ወጥቶ እየገፈፈ
እግዚአብሔር ቀድሞ እያለፈ
በርስቴ ላይ የተመሰጉት
እግዚአብሔር በኃይሉ ሲበትን
አዝማች · Chorus
ሁሉን በእጄ አሳልፎ ሰጥቶኛል
እድል ፈንታዬ ጌታ ሆኖልኛል (፪x)
አሃ አሃ እኔስ አልፈራ
አሃ አሃ አልደነግጥ (፪x)
እርሱ እየሄደ ከእኔ ፊት ፊት
እርሱ እየመራ ከእኔ ፊት ፊት
እርሱ እየወጣ ከእኔ ፊት ፊት
እየቀደመ ከእኔ ፊት ፊት
እኔስ አልፈራ አልደነትጥ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ጥላቸው ወጥቶ እየገፈፈ
እግዚአብሔር ቀድሞ እያለፈ
በርስቴ ላይ የተመሰጉት
እግዚአብሔር በኃይሉ ሲበትን
ሁሉን በእጄ አሳልፎ ሰጥቶኛል
እድል ፈንታዬ ጌታ ሆኖልኛል (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ