እግዚአብሔር ማንንም ጥሎ አያውቅም
Egziabhier Manenem Telo Ayawqem
ትራክ 8 · 5:41 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ብዙ ተዓምራቶችን ሲሰራ ያያችሁ
ሁልጊዜ በቃሉ እንዲህ ሲናገራችሁ
ማነው እንደ ኢየሱስ/ጌታ የሚሆንላችሁ
በመከራው ጌዜ ከእርሱ የሸሻችሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ማንንም ጥሎ አያውቅምና
ቸርነት ምህረቱ ከሕዝቡ ጋር ነውና
የመረጠህ አምላክ አይተውህምና
አንተም በጊዜውም አለጊዜውም ጽና
ቁጥር 2 · Verse 2
ቅዱሳኖች ጽኑ ጨለማው ይነጋል
ኢየሱስ ሲያስበን ሁሉም ነገር ያልፋል
ፀሐይ ሲወጣበት ተኖ እንደሚጠፋ
ቀናችን ይሄዳል ያስቆረጠን ተስፋ (፪x)
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ማንንም ጥሎ አያውቅምና
ቸርነት ምህረቱ ከሕዝቡ ጋር ነውና
የመረጠህ አምላክ አይተውህምና
አንተም በጊዜውም አለጊዜውም ጽና
ቁጥር 3 · Verse 3
እግዚአብሔር ከልቡ አያስጨንቀንም
ሕዝቡን ለተኩላዎች አሳልፎ አይሰጥም
ቢያሳዝነን እንኳን ልቡ ሚራራ ነው
ከእርሱ ጋራ መስማማት ያ ነው የሚሻለው (፪x)
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ማንንም ጥሎ አያውቅምና
ቸርነት ምህረቱ ከሕዝቡ ጋር ነውና
የመረጠህ አምላክ አይተውህምና
አንተም በጊዜውም አለጊዜውም ጽና
ቁጥር 4 · Verse 4
ክለቅሶ ከሃዘን ከማማረር ሕይወት
ክውድቀት ከድካም ፈጥኖ ሚያነሳበት
የጠፉትን ሁሉ የሚፈልግበት
እግዚአብሔር ጊዜ አለው የሚጐብኝበት (፪x)
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ማንንም ጥሎ አያውቅምና
ቸርነት ምህረቱ ከሕዝቡ ጋር ነውና
የመረጠህ አምላክ አይተውህምና
አንተም በጊዜውም አለጊዜውም ጽና (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ