ጽዮን ሆይ ተነሺ
Tsion Hoy Teneshi
ትራክ 3 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የምሬት ጊዜ የአምባ ጊዜሽ
ያንን መከራ ጉስቁልናሽ
ተመልክቶታል በቃ አታልቅሺ
ዘምሪ ዕልል በይ ጽዮን ተነሺ (፪x)
ጽዮን ሆይ ተነሺ
አዝማች · Chorus
ጽዮን ሆይ ተነሺ ዉለታውን አትርሺ
ይበቃል የለቅሶ ዘመን እምባሽን አብሺ
ያንን ክፉ ዘመን በማን ተሻገርሽ
አሁንም ሊረዳሽ ታማኝ ነው ጌታሽ
ቁጥር 2 · Verse 2
የእግዚአብሄር ጆሮዎች ጸሎትሽን ሰምተዋል
አንቺን ለማዳን እጁን ዘርግቷል
ያንን መከራ የሚያስረሳሽ
ይዞልሽ መጥቷል ድንቅ በረከቱን (፪x)
አዝማች · Chorus
ጽዮን ሆይ ተነሺ ዉለታውን አትርሺ
ይበቃል የለቅሶ ዘመን እምባሽን አብሺ
ያንን ክፉ ዘመን በማን ተሻገርሽ
አሁንም ሊረዳሽ ታማኝ ነው ጌታሽ
ቁጥር 3 · Verse 3
ትላንት በለቅሶ ለዘራሺው ዘርሽ
መጥቶልሻል ጌታ በሳቅ ሊያሳጭድሽ
ያኔ በመከራሽ የገባልሽን ቃል
ጌታ ሊፈጽመው ከማደሪያው ነቅቷል (፪x)
አዝማች · Chorus
ጽዮን ሆይ ተነሺ ዉለታውን አትርሺ
ይበቃል የለቅሶ ዘመን እምባሽን አብሺ
ያንን ክፉ ዘመን በማን ተሻገርሽ
አሁንም ሊረዳሽ ታማኝ ነው ጌታሽ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ