Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ርሆቦት

Rehobot

ትራክ 5 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እስከሚያውቁኝ የተጣሉኝ ሁሉ

አስፍቶኛል ጌታ እንደ ቃሉ

እኔም በዝቻለሁ ደስ ብሎኛል

ፍሬዬም አብቦ ይሄው ይታያል

እንዲያ ያሳደዱኝ ጠላቶቼ

ለመሆን ፈለጉ ወዳጆቼ

እርሆቦት ጌታ ስላሰኘኝ

እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው አለኝ

ሮሆቦት (፪x) እግዚአብሔር አስፍቶልኛል

መሻቴንም ፈጽሞልኛል (፪x)

የገባልኝን ቃል እይፈጽምም

ብዬ ተናግሬ ከቶ አይሆንም

ባልኩኝ ጊዜ እግዚአብሔር ትቶኛል

ርሆቦት ጌታ አስፍቶልኛል

ዛሬ አቁሞኛል በተራራ

አሳልፎ ያንን ሁሉ መከራ

እኔም እነግራለሁ በረከቴን

ያደረገልኝን መድሃኔቴን

ሮሆቦት (፪x) እግዚአብሔር አስፍቶልኛል

መሻቴንም ፈጽሞልኛል (፪x)

አሁን ግን ጽዋዬ ተርፎልኛል

እስክረሰርስ ድረስ ሞልቶልኛል

ከእንግዲህ በኋላ ከቶ አልጐድልም

በረከት አድርጐኛል ለዚህ ዓለም

የገባልኝን ቃል አይፈጽምም

ብዬ ተናግሬ ከቶ አይሆንም

ባልኩኝ ጊዜ እግዚአብሔር ትቶኛል

ርሆቦት ጌታ አስፍቶልኛል

ሮሆቦት (፪x) እግዚአብሔር አስፍቶልኛል

መሻቴንም ፈጽሞልኛል (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ