መፈታቴን አውጃለሁ
Mefetatien Awejalehu
ትራክ 1 · 4:41 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ችግር መከራዬን ብሶቴን የምታውቅ፤
የሚረዳኝ የለም ከእኔ አትራቅ
ለአንድ አፍታ ከልቤ ይሄንን ብነግረውን
ቀኜን ያሰረውን ገመዴን በጠሰው (፪x)
አዝማች · Chorus
መፈታቴን አውጃለሁ ለጠላቴም እነግረዋለሁ
በበጉ ፊት እሆናለሁ የድል ዜማን አዜማለሁ
በሕዝቡ ፊት አክብሮኛል ራሴን በዘይት ቀብቶኛል
አከብረው ዘንድ ይገባኛል አሜን
ቁጥር 2 · Verse 2
ኃይለኛና ታላቅ ነገር አደርጋለሁ
በእውነት የታመነ ቤትን እሰራለሁ
ታማኙ አምላኬ እንደተናገረው
በእርግጥ አድርጐታል ስሙን አከብራለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
መፈታቴን አውጃለሁ ለጠላቴም እነግረዋለሁ
በበጉ ፊት እሆናለሁ የድል ዜማን አዜማለሁ
በሕዝቡ ፊት አክብሮኛል ራሴን በዘይት ቀብቶኛል
አከብረው ዘንድ ይገባኛል አሜን
ቁጥር 3 · Verse 3
ናቡከደነጾር የተባለው ንጉሥ
ዓይኖቹን አንስቶ ከሰራዊት ቅዱስ
ባቢሎንን አይቶ በትዕቢት ታሰረ
ለሰባት ዘመናት ምድረ በዳ ቀረ
ዓይኖቹን አንስቶ እግዚአብሔርን ሲያየው
ወደ ቀድሞው ሕይወት ለክብር መለሰው
ይህንን ላደረገው ለታላቁ ጌታ
ምሥጋናን እንስጠው በዕልልታ በሆታ (፪x)
አዝማች · Chorus
መፈታቴን አውጃለሁ ለጠላቴም እነግረዋለሁ
በበጉ ፊት እሆናለሁ የድል ዜማን አዜማለሁ
በሕዝቡ ፊት አክብሮኛል ራሴን በዘይት ቀብቶኛል
አከብረው ዘንድ ይገባኛል አሜን
ቁጥር 4 · Verse 4
እስራትን ፈቶ ቀንበር የሰበረ
በሰማይ በምድር በጣም የከበረ
ፍጥረታት በሙሉ ሚታዘዙለት
ለበጉ ለኢየሱስ ክብር ይሁንለት (፪x)
አዝማች · Chorus
መፈታቴን አውጃለሁ ለጠላቴም እነግረዋለሁ
በበጉ ፊት እሆናለሁ የድል ዜማን አዜማለሁ
በሕዝቡ ፊት አክብሮኛል ራሴን በዘይት ቀብቶኛል
አከብረው ዘንድ ይገባኛል አሜን (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ