Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አትቸኩልም አንተ

Atechekulem Ante

ትራክ 11 · 5:34 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ጥቂት ጊዜ አለፈ ከተናገርካቸው

አብርሃምና ሳራን ተስፋ ፈተናቸው

ከዚህ የተነሳ እርምጃን ወሰዱ

አንተንም ቀደሙ እስማኤልን ወለዱ

ግን አንተ ጌታችን ስለተስፋህ ብለህ

ይስሐቅን አምጥተህ ቃልህን ፈጸምህ (፪x)

አትቸኩልም አንተ ደግሞም አትዘገይም

ቀስ እያልክ ብትሄድ ማንም አይቀድምህም

ነገርን በሙሉ በጊዜው ውብ አድርገህ

በድንቅ በተዓምራት ታበጃጀዋለህ

ክብርህን ትገልጻልህ

ወንድሞቹ ሲሰግዱ ዮሴፍ ህልምን አየ

ግን የኖረው ኑሮ ከዚህ የተለየ

ቃልህ እስኪመጣለት እርሱም ተፈተነ

በእርኩሰት በኃጢአት ላይ ሁሌ እየጨከነ

የሚጐበኝበት የእግዚአብሔር ቀን መጣ

ከእዛ ጉስቁልናው ከመከራ ወጣ (፪x)

አትቸኩልም አንተ ደግሞም አትዘገይም

ቀስ እያልክ ብትሄድ ማንም አይቀድምህም

ነገርን በሙሉ በጊዜው ውብ አድርገህ

በድንቅ በተዓምራት ታበጃጀዋለህ

ክብርህን ትገልጻልህ

ሃና መካኗ ሴት ብዙ አለቀሰች

በወገኖች ሳይቀር እየተነቀፈች

እርሷም እንደ ሰዎች ዘመኗ ደረሰ

ልቧ በአንተ ጸና ታሪኳም ታደሰ

አቤት የእግዚአብሔር ስራው ያስደንቃል

የምስኪኑን እንባ በጊዜው ያደርቃል (፪x)

አትቸኩልም አንተ ደግሞም አትዘገይም

ቀስ እያልክ ብትሄድ ማንም አይቀድምህም

ነገርን በሙሉ በጊዜው ውብ አድርገህ

በድንቅ በተዓምራት ታበጃጀዋለህ

ክብርህን ትገልጻልህ

በጣም የምትወደው አልዓዛር ታሟል

የሚል ድምጽ ከሰማ አራት ቀን ሆኖታል

የሞተውን ሊያስነሳ እንባቸውን ሊያብስ

በራሱ ጊዜ መጣ ጌታችን ኢየሱስ

ዛሬም ብንጠብቀው በመጠበቂያችን

እግዚአብሔር ቅርብ ነው ክብሩን ሊገልጽልን (፪x)

አትቸኩልም አንተ ደግሞም አትዘገይም

ቀስ እያልክ ብትሄድ ማንም አይቀድምህም

ነገርን በሙሉ በጊዜው ውብ አድርገህ

በድንቅ በተዓምራት ታበጃጀዋለህ

ክብርህን ትገልጻልህ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ